ቦሌ መድኃኔዓለም የሚገኘዉ አቢሲንያ ባንክ ዛሬ ምሽት ተዘረፈ

ቦሌ መድኃኔዓለም የሚገኘዉ አቢሲንያ ባንክ ዛሬ ምሽት ተዘረፈ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በአዲስ አበባ  ቦሌ  መድኃኔዓለም  የሚገኘዉ አቢሲንያ ባንክ ዛሬ ምሽት መዘረፉ ተገለጸ። በሀገር ውስጥ የሚሰራ ”ካፒታል ጋዜጣ” የተሰኘ እንግሊዝኛ ጋዜጣ እንደዘገበው ማንነታቸው ያልታወቁ ስድስት ዘራፊዎች ወደ ባንኩ ዘልቀው በመግባት 5 ሚሊዮን ብር መዝረፋቸውን ገልጿል።

በባንኩ ቅጥር ግቢ የነበሩ ስድስት ተሽከርካሪዎችም መውደማቸው ተገልጿል። ሁለት ተጠርጣሪዎች መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን ቀሪዎቹን ለመያዝ አሰሳ እየተደረገ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የአብሲያኒ ባንክ ሰራተኞች ለጋዜጣው በሰጡት ቃል፤ ዘራፊዎቹ  ድርጊቱን  የፈፀሙት ከጥበቃ ሰራተኞች ጋር  በመሻረክ እንደሆነና በጦር መሳሪያ ሰራተኞችን በማስፈራራት እንዲሁም እገታ በመፈፀም እንደሆነ አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ የባንክ ዘረፋ ሲካሄድ ከረጅም ዓመታት በኃላ መሆኑ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY