የኦህዴድ ስምንተኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቀቀ

የኦህዴድ ስምንተኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቀቀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኦህዴድበአዳማ ከተማ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ድርጅታዊ ኮንፈረንስ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት የሚችል ብቁ አመራሮችን ለማፍራት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንክሮ እንደሚሰራ በመግለፅ ዛሬ ከሰዓት ተጠናቋል። ድርጅቱ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅም ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

ድርጅቱ ባወጣው የአቋም መግለጫ ላይም “ጎሰኝነትንና አክራሪነትን በመዋጋት የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ በማድረግ የአብሮነትና ሀገራዊ ስሜት በህብረተሰቡና በአመራሩ ዘንድ እንዲጠናከር ለማድረግ እንደሚሰራ” ተገልጿል።

በዶክተር አብይ በቀድሞ ቦታቸው የተተኩት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሜቴ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አዳነች ሀቤቤ “የኦሮሞ ህዝብ ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ መሰረት ነው” በማለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የጽ/ቤት ሀላፊዋ አያይዘውም ክልሉ ያለውን ራዕይ ሀገራዊ በማድረግ በአንድ መንፈስ የመስራት ባህል እንዲዳብርም ጥሪ አቅረበዋል።

ኦህዴድ በተሃድሶ ግምገማ አነስተኛ ውጤት ያስመዘገቡና ያልተገባ አሰራርን የተከተሉ ከ3000 በላይ አመራሮች ከድርጅቱ አባልነት መሰረዛቸው ተገልጿል።

የተወሰነ ጉድለት የታየባቸው  1500 አመራሮች ከሀላፊነት (ስልጣን) የተነሱ ሲሆን  536 አመራሮች ደግሞ ከደረጃቸው ዝቅ ብለው እንዲሰሩ መደረጉንም  የጽ/ቤት ሀላፊዋ አስረድተዋል። በምትኩም ከ2000 በላይ ወጣቶች ወደ አመራርነት ቦታ መምጣታቸው ታውቋል።

 

LEAVE A REPLY