ዴርቶጋዳ – ደራሲ፤ ይስማዕከ ወርቁ ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ

ዴርቶጋዳ – ደራሲ፤ ይስማዕከ ወርቁ ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ

አንባቢ ሆይ! ዴርቶጋዳን ጨምሮ አስራ ሶስት መፃህፍትን ያበረከተው ተዓምረኛውና ምጡቁ ወጣት ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ በደረሰበት አስከፊ አደጋ መናገር አይችልም። የሁለት ህፃናት አባት የሆነው የሥነ ፅሁፍ ጠቢብ ገና የሰላሳ አንድ ዓመት ወጣት ነው። ይስማዕከ ደራሲ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ቅርስ ነው። ይህ ቅርስ ስለ ኢትዮጵያና ቅርሷ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጊዜ ሊደርስለትና በቅርስነቱ ሊታደገው በረከቶቹ ግድ ይሉናል። ይስማዕከን ኢትዮጵያም ልታክመውና ልታድነው የእናትነት ግዴታም አለባት። ይስማዕከን ማዳን የዚህን ወጣት ትውልድ ራዕይም ማዳን ነው!! እነሆ ወጣቱ ብላቴና የሥነ ጥበብ ፈርጥ የሚገኝበትን ዕውነታ ከቅኝቱ መጨረሻ የሚገኙትን ቪዲዮዎች ጊዜ ወስደው ይመለከቷቸውና የበኩልዎን ይወስኑም ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ።

ይስማዕከ  ሆይ በርታ፤ ዕምነት ተስፋና ፍቅር ያድኑሃል!!

     {ይህ ቅኝት በሰኔ 2002 ዓ/ም (ጁን 2010) ተፃፈ}

 መነሻ

                                                                                                                                                  ዴርቶጋዳን በማንበቤ ሠላምአጥቼ ሰነበትኩ። ነፍሴም በከፍተኛ ማዕበል ስትናወጥከረመች። ውስጠቴን የዘለቀ ጥልቅ ሀዘን ደግሞም ደስታደግሞም ብሩህ ራዕይ ተፈራረቁብኝ።  ማዕበሉ ፀጥ ሲልነፍሴም መልህቋን ስትጥልለብዙ ማዕልትና ሌሊትበጥሞና  አሰላሰልኩ። ከነፍሴ ጋር ተማከርኩ። እርግጥ ነውየዴርቶጋዳ ምሥጢረ ምሥጢራት ሁሉ  ገናአልተገለጡልኝም ይሆናል። ነፍሴ ግን መተንፈስ  ፈለገች፤ከጭንቀቷ መገላገል፤ ስለዴርቶጋዳ መናገር። እና ብዕሬንአነሳሁ። እነሆ ዴርቶጋዳን ከአንባቢያን ጋር መጋራትፈለግሁ። ስለምን ደካማዋ ነፍሴ ታፍና ትሙት?! እንግዲህ አንባቢም ይህንን ፅሁፍ አስጀምሮ ያስጨርሰው ዘንድትዕግስቱ ይሁን! እነሆ ዴርቶጋዳ

 እኛም አለንዳን ብራውን!

ዳን ብራውንን ስሙን ያልሰማ ወይም ከመፃህፍቱያልተቋደሰ ይኖር ይሆን? ብራውንየዳቪንቺ ኮድደራሲነው። ይህ ቅኝት በተፃፈበት ሰሞን ካሳተመው ሎስትሲምበልጋር አምስት መፃህፍትን አቅርቦልናል። ብራውንየደራሲ ሮበርት ሉድለም ደቀ መዝሙር ነው። ሉድለምበአርባ አመቱ ወደ ድርሰት ዓለም ከገባ በሁዋላ በህይወትበኖረባቸው ዘመኑ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ውስብስብ፤እጅግ ፈጣን የድርጊት ታሪክና የደም ዝውውወርን የማቆምሃይል ያላቸው የሚመስሉ ልብ አንጠልጣይ የስለላና የሴራመፃህፍትን አበርክቶልናል።

 ደቀመዝሙሩን ከመምህሩ (ብራውንን ከሉድለም) የሚለየው ጉልህ የድርሰት ባህሪ አለው። አንባቢየብራውንን መፃህፍት አንብቦ ሲጨርስ ነፍሱ እፎይታንአታገኝም። ሠላም አይኖራትም፤ ዕውቀት ትጠማለችና። ይህየብራውን ልዩ የድርሰት ችሎታው ነው። ይህ የዳን ብራውንየድርሰት አደራረስ ልቤን ምርኮኛው አድርጎት ኖሯል።

 ለምሳሌ በብራውን መፃህፍት ሳቢያ –  በቫቲካን ቁልፍልፍኮሪደሮችና በከርሰ ምድሩም የምሥጢር ጓዳ ጉድጓዶች፤በፓሪስ ጥልፍልፍ መንገዶችና ሙዚየሞች፤ በስፔንካቴድራሎችና በስዊስ የባንክ ጎተራዎች፤ በኒውዮርክጉራንጉሮችና በዋሽንግተን ድብቅ ዋሻዎች….የሊዮናርዶዳቪንቺን ሥዕላዊ ምሥጢራት፤ የኒውተንን ድብቅ ቀመር፤የገጣሚያንን ስውር ቅኔ፤ የመንግሥታት መሪዎችን ስውርተልዕኮየባህታውያንን፤ የቴምፕለሮችን፤ የማሶናውያንንምሥጢራዊ ድርጅቶችና ዓላማዎችቻቸውንብራውንንተከትዬ ሳሳድድና አብሬያቸው ስሳደድ ኖሬያለሁ።ከእንግዲህስ ነፃነቴን አውጃለሁ አቶ ዳን ብራውን!

 ፀሐይ በጠዋት ማልዳ አዲስ ቀን መውጣቱን ለአዳም ዘርለማብሰር አድማስን ታካ ከወደ ምሥራቅ አምራና ደምቃፍንትው እንደምትል፤ እንዲሁ ደግሞ ከወደ ምሥራቅአፍሪቃ ከምድረ ኢትዮጵ  በዓለም የሥነ ፅሁፍ ማማ ላይየወጣ ዴርቶጋዳ ርችቱን ተኩሷል። ተኳሹም ብላቴናይስማዕከ ወርቁ ይባላል።

 ዴርቶጋዳበሴራው ውቅረት የረቀቀ፤ በቋንቋው ውበትየመጠቀ፤ በገፀ ባህሪያቱ የገዘፈ፤ በምናብ ህዋን የዳሰሰ፤ተስፋና ራዕይ ያነገበ፤ ትላንት ዛሬንና ነገን ያቆራኘ፤ የዚህወጣት ትውልድ ታላቅ የሥነ ፅሁፍና የፈጠራ ስራ ውጤትነው፤ ብላቴናው ይስማዕከ ወርቁ በረከት።

 እነሆ በፓሪስ ኤፍል ታወር ላይ ቆሜ፤ በኒው ዮርክ ስታቹ ኦፍሊበርቲ ሠገነት ላይ ወጥቼ፤ በሲድኒ ሀርበር ብሪጅ ላይተንጎራድጄ፤ አዲስአባ በምኒልክ አደባባይ ነጋሪት ጎስሜዴርቶጋዳን ለዓለም አውጃለሁእኛም አለን ዳን ብራውን!!

 ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝ

 በታላቁ መፅሐፍ ላይ ኢትዮጵያ ስሟ ተደጋግሞ ተነስቷል።ከሁሉም በላይ ግን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አያሌ የዓለምማህበረሰብንም አመራማሪውኢትዮጵያ እጆቿን ወደፈጣሪ ዘርግታለች የሚለው ነው።

 ይህ ከተፃፈ ምዕተ ዓመታት ተቆጥረዋል። ዛሬም ኢትዮጵያእጆቿን ወደ ፈጣሪዋ እንደዘረጋች ናት። ፀሎቷንናልመናዋን አላቋረጠችም።አንኳኩ ይከፈትላችዃል፤ እሹታገኙማላችሁይላል የጌታ ቃል። ኢትዮጵያ እስከዛሬባላቋረጠችው ፀሎቷ የምትሻውን አላገኘችም። በሩምአልተከፈተላትም።

 ለመሆኑ ስለምን ይሆን ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪዋዘርግታ የምትፀልየው? ፀሎቷስ ስለነማን ነው? ፈጣሪዋስየሚሰማት መቼ ይሆን?…እንጠይቃለን እኛ።

 እነሆ አንድዬ ፀሎቷን መስማቱንና የዛሉት ክንዶቿምይጠነክሩ፤ የጠወለገው ገላዋም ይፋፋ፤ ግርማ ሞገሷምይመለስ ዘንድ፤ ራዕይ አስይዞ መልዕክተኛውን ልኮላታልዴርቶጋዳን።

 እንደ መልዕክተኛው ጳውሎስም፤ ራዕይ የታየው ብላቴናውመልዕክተኛ ይስማዕከ ሲፅፍም፤ ከላይኛው ደራሲ ዘንድየተላከ ታላቅ መልዐክ በሬን በርግዶ ገብቶ ከእንቅልፌአባነነኝ።ከወርቃማ ክንፉ ላይ አንድ ላባ ነቅሎ ብዕርቀርፆ ሰጠኝ። በታላቅ ሰሌዳ ላይምማሔር ሻላል ሐሽባዝብለህ ፃፍ አለኝ።…” ይላል።  ምን ማለት ይሆን? ይህየስላሴ ቋንቋ ነውን? ራዕይ የታያቸው ብቻየሚገለጥላቸው?

 በላይኛው መልዐክ ቋንቋ ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝማለትም ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛ ቸኮለ ማለት ነው ይለናልምሥጢሩን የፈታልን ይስማዕከ።

 ተማራኪው ማን ነው? ተበዝባዡስ? ብዝበዛውስ መፍጠኑስለምንድን ነው? – እንላለን እኛ ደግሞ፤ ምሥጢራዊውቋንቋ ይበልጥ በአእምሯችን እየተወሳሰበ።

 ኦርያ ኢትዮጵያማሔር ሻላል ሐሽ ባዝይላልደራሲው ደግሞበውድቅት ሌሊት የተነገረውን መልዕክትሲያስተላልፍልን። ምን ማለት ነው? እንጠይቃለን እኛደግሞ።ኦርያ!…ማሔል ሻላል ሐሽ ባዝማለትምየኢትዮጵያ ተባዮች ከላይዋ ላይ ተነሱምርኮፈጥኗልብዝበዛ ቸኩሏልማለት መሆኑንተርጉሞልናል ደራሲው።

 ያንተ ያለህ! እንላለን እኛ፤ መልዕክቱ እንደ ድንገተኛነጎድጓዳዊ መብረቅ በህሊኛችን ውስጠ ውስጥ ብርሃኑሲያስገመግም እየታየን።ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮአላቸው አይሰሙምየሚለው የመለኮት ቃልከነጎድጓዳዊው ብርሃን ጋር በአእምሯችን እያስተጋባ።

 ዕውነት ነው እንላለን፤ የጋረደን ጉም እየተገለጠልን፤ዕውነታው እየታየን። ኢትዮጵያ በተባዮች ተወራለች።ኢትዮጵያ ተማርካለች። እጆቿንም ወደ ፈጣሪ እንደዘረጋችያለችው ዛሬም መማረኳን ስታሳየው ነው፤ አቅም ማጣቷን፤ከምርኮዋ ነፃ የሚያወጣት አለማግኘቷን።

 ኦርያ ኢትዮጵያ!”

 ዕርግጥ ነው አይተናል። ዕውነት ነው ሰምተናል። ብዝበዛውፈጥኗል። የኢትዮጵያን ሆድዕቃ ቦትርፈው አንጀቷንየሚዘለዝሉ ጅቦች በዝተዋል። እነሆ እንደ መስቀልቅርጫም እየተቀራመቷት ናቸውና። ለዘመናት አይተንእንዳላየሰምተንም እንዳልሰማ ኖረናል። ሀጢያታችንበዝቷል። ወንጀላችንም በርክቷል። እንደ ጲላጦስእጆቻችንን ታጥበንበኢትዮጵያ ምርኮ የለንበትም፤ብዝበዛውንም አናውቅምለማለት አንችልም። የፍርድቀን ቀርቧልና!

 ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝእግዚአብሄርም ታላቅ ሰሌዳወስደህ ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛ ቸኮለ ብለህ በሰው ፊደልፃፍበት። የታመኑትን ሰዎች ካህኑን ኦርዮንና የበራኪዩንልጅ ዘካርያስን ምስክሮች አድርግልኝ አለኝይላል የኢሳያስመፅሀፍ። ይህ እንግዲህ የናሳው ሳይንቲስት ኢንጂነር ሻጊዝእጅጉ በዴርቶጋዳ ላይ ለትንሳኤ ኢትዮጵያ ያዘጋጀው /ሚራዥ በቀይ ድንጋይ ላይ ተቀርፆ የደረሰው መልዕክትመፅሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉም ነው።

 አዎንአለ ሚራዥ ቀዩን ድንጋይ እንደያዘ፤ ምርኮፈጥኗል ብዝበዛም ቸኩሏል። ሀገሪቱ በቅጥረኞችናበአድርባዮች እየተበዘበዘች ነው። ህዝቦቿ የበይተመልካች ሆነዋል። ተስፋ በቆረጠ ትውልድተሞልታለች። ወጣቶቿ እንጀራ ፍለጋ በባዕዳን ሀገርሲሰደዱ በጋንጃቸው እየታረዱ ነው። ሴት ልጆቿ የአረብገረዶች እየሆኑ ነው። ማምለጫ ያጡትም በጥቁርአልማዛቸው ላይ ተኝተው እየለመኑ ነው። አዎ ጥቂቶችእየበዘበዙ ነው። ኢትዮጵያን የተሰበረ መንፈስወጥሯታል። ምርኮ ፈጥኗል ብዝበዛም ቸኩሏል።

 ያንተ ያለህ! እንላለን እኛ ይህንን ስናነብ  ከሚያስጨንቅህልም ውስጥ ድንገት እንደ ባነንን ሁሉ። ምርኮውመፍጠኑ ብዝበዛውም መቻኮሉ ስለምን ይሆን? እንላለንበአንክሮ። ምን ይሻላል? ምን ይበጃል? አርባ ማዕልት አርባሌሊት ብንፆም ብንፀልይና ብንሰግድ ፈጣሪያችን ይታረቀንይሆን? – እንጠይቃለን እኛ።

 የለም! ይለናል ዴርቶጋዳ። ፆም ፀሎት ለነፍሳችሁ ነው፤ለሥጋችሁ። እና ምን ይሻለናል? እንጠይቃለን ደግመን።

 አንድ ነገር ያስፈልጋል። ለለውጥ ራስን መስጠት።አሁንምኢትዮጵያ አንድ አብዮት ያስፈልጋታል።ልጆቿን የማይበላ አብዮት! ራሱን የማይውጥ አብዮት! ሳይንቲፊክ ሪቮሉሽን። በሳይንስና ቴክኒዮሎጂ የታገዘአብዮት።ለውጥን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ የለም። ለውጡሆዳቸውን ከሚያጎልባቸው ጥቂቶች በቀር። ችግሩ ግንየለውጡ አካል መሆን የሚፈልግ የለም። በሌሎች ሞትናደም ለመጠርቃትና ኑሯቸውን ለማደላደል የሚመኙብዙዎች ናቸው።ከዓለማችን ዝነኛ ሳይንቲስቶች አንዱሻጊዝ እጁጉ ነው የሚመልስልንበዴርቶጋዳ።

 ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ግራ በመጋባት እንጠይቃለን።ከሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን ሰቆቃው ጴጥሮስምሥጢራዊ ሥነ ግጥም ውስጥ መልሱን ታገኙታላችሁይለናል ዴርቶጋዳ።

 1961 / አባ ዲዲሞስ የተባሉ ሰው ለባለ ራዕዩ ወጣትገጣሚ ፀጋዬ ገብረ መድህን በአቁማዳቸው ውስጥ ከያዙትብራና አርባ ስምንት ቃላትን አውጥተው አንድ መቶአምስት (105) ስንኞች ባሉትሰቆቃው ጴጥሮስሥነግጥሙ ውስጥ ወጣቱ ባለቅኔ እንዲዘራቸው ያደርጉታል።አርባ ስምንቱን የአባ ዲዲሞስ ምሥጢራዊ ቃላት ጨምሮሰቆቃው ጴጥሮስአራት መቶ ዘጠና ሰባት (497) ቃላትአሉት። እነሆ እኒህ አርባ ስምንት ቃላት ታላቅ ምሥጢርያለውንና በቁጥሮች የተነቀሰውን ፊደል ቅርፅየተሰራውን ዴርቶጋዳየተሰኘውን መስቀል እንቆቅልሽየሚፈቱ ቁልፎች ናቸውይለናል ይስማዕከ ወርቁ። ታምርአያልቅም፤ በዴርቶጋዳ! ለመሆኑ አባ ዲዲሞስ ማን ናቸው? እንጠይቃለን እኛ።

 አባ ዲዲሞስ የአባ ፊንሀስና የአባ ዠንበሩ ጓደኛ የነበሩየማፊያው የአባ ዲዎላ አባትበሳይንቲስት ሻጊዝ እና በዶ/ ሚራዥ ጀርባ ላይ የሚገኙትን የመስቀል ንቅሳቶችየሳሉአቡነ ጵጥሮስ ሀውልት ላይ ሽንታቸውንእያንፎለፎሉ አቡኑን ሲሳደቡከወጣቱ ባለቅኔ ፀጋዬ ጋርግብግብ የገጠሙ ናቸው፤ አባ ዲዲሞስ ማለት።

 ስለምንድን ነው አባ ዲዲሞስ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ላይመሽናታቸው? የከረመ ብስጭት አለባቸውአባ ዲዲሞስ።አቡነ ጴጥሮስ አልሰማ ብሎኝ ነው የሞተውይላሉ አባዲዲሞስ።ክፉ ነገርን ማለፊያ ጥበብ አልነገርኩህምነበር?…አንተ ድንጋይ!…ክፉ ቀንን በጥበብ ከማለፍ በላይጥበብ የለምይህንንም ነግሬህ ነበር። ይህቺ ደም መላስየለመደች ሀገር የምትለወጥ መስሎሃል!ስንት ጀግኖችሞቱላትአልተለወጠችም። ጴጥሮስ አልነገርኩህምአንተብትኖር ኖሮ ይሄኔ አቡነ ዲዲሞስ እባል ነበር። የዚህች አገርእጣ ፈንታ በእጃችን ይወድቅ ነበር። እንለውጣት ነበር። ግንሞትክጵጵስና ሳትሾመኝ ሞትክይህን እያሉ ነበር አባዲዲሞስ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ላይ ሽንታቸውንያንፎለፎሉት1961 /ም።

 ይህንን ስናነብ አእምሯችን ይወጠራል። አቡነ ጴጥሮስና አባዲዲሞስ ይተዋወቁ ነበርን? ምሥጢርም ነበራቸው ማለትነው? ኢትዮጵያን የመለወጥ ምሥጢር? ለመሆኑ አቡኑናአባው ኢትዮጵያን የመለወጥ ራዕያቸው ምን ነበር? ሃይማኖትና ፖለቲካ፤ ጉድ ነው! እንላለን በመሃይምአንደበታችን፤ እንቆቅልሹ ሲበዛብን።

 ይኸው እኒህኛው ጳጳስ የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም አበምኔትእንኳ ያድርጉኝ ብላቸው ከለከሉኝ። አባ ዠንበሩን ሾሙት።አንተ ብትኖር ግን ወንበዴዎች ጳጳስ ሆነው አይሾሙምነበር። እኔና አንተ የምናውቀው የዚህች ሀገር ምሥጢርበወንበዴዎች እጅ አይገባም ነበር።ለምን ስልጣንሳትሰጠኝ ሞትክ? ለዚህች ሀገር ታላቅ ስራ ልንሰራተስማምተን ከዳኸኝ አንተ ድንጋይ…” ማርያም ድንግላዊትሆይ! እባክሽ አማልጂን! እንላለን ስድስት ጊዜ አማትበንበአባ ዲዲሞስ ንግግር ተጨንቀን።

 ጵጵስናውንም ወንበዴዎች ተሹመውበታል እንዴ?እግዚኦ!! ይህ ሁሉ ሲሆን  ኢትዮጵያውያን የት ነበርን?  ለመሆኑ አባ ዲዲሞስና አቡነ ጴጥሮስ ይጋሩት የነበረውየዚህች ሀገር ምሥጢርስ ምንድን ነበር? እንጠይቃለንራሳችንን ደጋግመን።

 ታዲያ አባ ዲዲሞስ ሀውልቱ ላይ መሽናታቸውና አቡነጴጥሮስን መሳደባቸው ሆን ብለው ነበር፤ ወጣቱን ባለቅኔናገጣሚ ፀጋዬ ገብረመድህንን አበሳጭተው ለማጥመድ።

 ድንጋይ አይደለምይላቸዋል ወጣቱ ገጣሚ በደም ፍላት፤አባ ዲዲሞስ ላይ አፍጥጦ። ድንጋይ ነውይሉታልእሳቸውም መልስው እያፈጠጡበት። ይቃመሳሉ በቡጢዲዲሞስና ፀጋዬ።ያን ሌሊት ፀጋዬ ቤቱ ሲገባ ሰቆቃውጴጥሮስ ይፅፋል። ያንኑ ሌሊት አባ ዲዲሞስም ፀጋዬ ቤትዘው ብለው ይገባሉ። እናም ያንኑ ሌሊት አቁማዳቸውንፈትተው ከብራናቸው ላይ አርባ ስምንት ቃላት ለወጣቱገጣሚ ሰጥተውት ሰቆቃው ጴጥሮስውስጥ አራምባናቆቦ አድርጎ እንዲዘራቸው አዘዙት። የቃላቱን ምሥጢርፀጋዬ አያውቅም። አውቆም ከነበረ አልነገረንም። ግንዝም እንበልብሎ ፅፏል፤አብረን ዝም እንበል ሌላቅኔ፤ ሌላ ቁልፍ፤ ሌላ ምሥጢር ይሆን? አናውቅም።ከእንግዲህእሳት ወይ አበባየሥነ ግጥም መድብልመሆኑ አከተመ፤ የምሥጢራት ጎተራ እንጂ! እድሜለዴርቶጋዳ፤ እድሜ ለብላቴናው ይስማዕከ!

 እሳት ወይ አበባ የሚለው የፀጋዬ የሥነ ግጥም መድብልለህትመትብርሃንና ሰላምሲገባ አባ ዲዲሞስአክሳፎስየሚል ርዕስ ያለው የመፅሀፍ ረቂቅ ይዘው ገብተው ነበር – “ሰቆቃው ጴጥሮስበመድብሉ ውስጥ መካተቱንና አርባስምንቱም ምሥጢራዊ ቃላት በግጥሙ ውስጥተሰራጭተው መኖራቸውን ለማረጋገጥ። አባ ዲዲሞስአክሳፎስ አላሳተሙም። ለመሆኑአክሳፎስምን ማለትይሆን? ማለታችን ግን አልቀረም። ማን ያውቃል? አንድ ቀንአክሳፎስታትሞ ምሥጢሩንም እናውቅ ይሆናል።እስከዛው ግን  ዴርቶጋዳምሥጢር እንመራመር

 አባ ዠንበሩ ራዕይ ናቸው

 አባ ዠንበሩ፤ አባ ዲዲሞስ፤ አባ ፊንሐስ። ሶስት አባዎች፤የዴርቶጋዳ ምሥጢር መዘውሮች። ሶስት አርበኞች።በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ዘመን የነፃነት ፋኖዎች።በምሥጢራት የተሞሉ አባዎች፤ አርበኞች። ከነፃነትበዃላስ?…

 “…ዋሻውን መቆፈር ስንጀምር (አባ ዠንበሩ፤ አባዲዲሞስ፤ አባ ፊንሐስ) አላማችን ለራሳችን መደበቂያነትለመጠቀም ነበር። በዃላ የሀገሪቱ ውድ ሀብቶችና የብራናመፃህፎች ከጥፋት መከላከያ ሆኖ አገለገለ። እኔም በዚህወቅት በገዳሙ ውስጥ በማነባቸው መፃህፍት እየተቀየርኩመጣሁ። ራዕዬን ከግለሰብነት ወደ ሀገራዊነትቀየርኩት…” አባ ዠንበሩ ናቸው ለዶ/ ሚራዥየሚነግሩት።

 አባ ዠንበሩ የዴርቶጋዳ ራዕይ ናቸው፤ እርሾ። የጣና ገዳማትጥንተ ጥንታዊ መፃህፍት ናቸው አባ ዠንበሩን ዳግምየፈጠሯቸውራዕይ የሰጧቸው። እንቀጥል የአባዠንበሩን ትረካ፤

 “…ይህንን ዋሻ ወደ ትልቅ ህቡዕ የምርምርና መንግሥታትሲለዋወጡ የማይለዋወጥ ለሀገሪቱ ፅኑ መሰረት የሚሆንምሥጢራዊ ድርጅት የማድረግ ራዕይ በውስጤተጠነሰሰኢትዮጵያን ለኢትዮጵያውያን ማድረግየሚቻለው ትክክለኛው የቴክኒዮሎጂ ዕውቀትናትክክለኛው የቴክኒዮሎጂ መሳሪያ በራሷ ልጆች እጅ ሲገባመሆኑን ተረዳሁ።ይህንን ራዕይ የተጋራኝ ሰው አለቃአያሌው ብቻ ነበር። አያሌውአባ ዲዲሞስ ይባል ነበር። አባዲዲሞስ ብዙ ለውጦች ለማምጣት ሥልጣን ይፈልግነበር።ከአቡነ ጴጥሮስ ጋር ቅርርቦሽ ነበረው።አቡነጴጥሮስ በባንዶች የጣሊያን አሽከሮች በጥይትተደብድበው ሞቱ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ባህሪውተለወጠብኝ።…” ይላሉ አባ ዠንበሩ ለዶ/ ሚራዥሲያስረዱ። አባ ፊንሐስስ?… “…አባ ፊንሐስ ስለ ሀገርማሰብ አይፈልግም። ኢትዮጵያ የሚለው ቃልያንገሸግሸው ነበርይላሉ አባ ዠንበሩ። አስገራሚታሪክሶስት አባዎችሶስት መንገዶች።

 አባ ዲዲሞስ፤ አርበኛ፤ ፈላስፋ፤ ንቅሳት (ንድፍ) ነዳፊ፤ለውጥ አላሚ፤ ሥልጣን ፈላጊ።

 አባ ፊንሐስ፤ ከራስ በላይ ንፋስ ያሉ፤ የኢትዮጵያን እንባመጥረግ እማይፈልጉ፤ ከዋሻው ውስጥ ከሚገኙት ቅርሶችየንጉሥ ዘውድ ሰርቀው የሸጡ፤ ወንጀለኛ አባ።

 አባ ዠንበሩስ? አባ ዠንበሩማ ራዕይ ናቸው ብለናል፤የኢትዮጵያ ራዕይ

 እንቀጥል

“…በዚህ ዋሻ ውስጥ ብዙ ለውጦች ታይተዋልይህምየሆነው እንደ ኢንጂነር ሻጊዝ ያሉ ኢትዮጵያውያንሳይንቲስቶች በገንዘብም በእውቀትም አብረውን መስራትከጀመሩ በሁዋላ ነው።…” ይላሉ አበ ዠንበሩ ለዶ/ሚራዥ ሲያብራሩ። አባ ዠንበሩ ምንድን ነው እሚነግሩን? ኢንጂነር ሻጊዝ እጅጉ፤ የናሳው ምርጥ ሳይንቲስት ከአባዠንበሩ ጋር? እንጠይቃለን በታላቅ መደመም፤ የዴርቶጋዳተአምር መቼም በዋዛ አያልቅም።

ከእኔ የሚጠበቀው ምንድን ነው?” / ሚራዥ ነበር አባዠንበሩን የጠየቃቸው።

ሁለት ነገር ይጠበቅብሃል። አንዱ ቀሪ ህይወትህን በዚህድርጅት ውስጥ በማገልገል ሀገርህን ከጥፋት ማዳንነው። በዚህ ሰዓት ዓለም ዐቀፍ ማፍያዎችከማይጠረቁት የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመሻረክሀገርህን እየበዘበዙዋት ነው።

ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝምርኮ ፈጠነ ብዝበዛ ቸኮለ።ኢትዮጵያ ተስፋ በቆረጡ ወጣቶችና ህዝቦችተሞልታለች። የብዙ ኢትዮጵያውያን መንፈስተሰብሯል። የድህነቱ ምንጭ ምን እንደሆነ ሁላችንእናውቀው ይሆናል። እሱን ለመድፈን ግን አንድ ልብየለንም። መንፈሳችን ተሰብሯል። ስለዚህም በአሰቃቂሁኔታ እየተበዘበዝን ነው። ራሳችንን ለብዝበዛያጋለጥነው እኛው ራሳችን ነን። የጋራ ራዕይ ሊኖረንይገባል።

አባ ዠንበሩ የሚነግሩት ለማን ነው? እንላለን። እያንዳንዱቃል በህሊናችን እየተሰነቀረ የሀገራችንን እውን ሰቆቃለዳተኛው ልባችን እየነገረ ማንነታችንን ሲፈትነንእየታወቀን። አዎ ዕውነት ነው፤ መንፈሳችን ተሰብሯል፤በዘመናችን የህወሃት ፕሮፓጋንዳና ተግባር ማንነታችንተሽመድምዷል፤ ወኔያችን ተሰልቧል፤ መሰረታችንተናግቷልምን ይሻላል? እንመለስ ወደ አባ ዠንበሩ፤

“… ሌላው ከእኔ የሚጠበቀው ነገር ምንድን ነው?” ጠየቃቸው / ሚራዥ።

የሰጠመውን መርከብ የምናወጣበትን ቁልፍ ስጠኝ

ምን?”

ቅርፅ የተሰራውን ግማደ መስቀል መልስልኝ።

እሱ መስቀል ቁልፍ ነበር እንዴ?”

ሰአሊነነ ቅድስት! ጉድ መጣ!! አባ ዠንበሩ ሰጠመ ያሉትመርከብ ምንድን ነው? እንላለን ልባችን እንደ ማዕበልእየተነሳና እየፈረጠ። ማንስ ለምን አሰጠመው? መቼስ ነበርየሰጠመው? በውስጡስ ምን ይዟል? መርከቡና አባዎቹስግንኙነታቸው ምን ይሆን? ግማደ መስቀሉስ እንደምንየሰጠመው መርከብ መክፈቻ ቁልፍ ሊሆን ይችላል? ለዶ/ሚራዥስ ቁልፉን ማን ሰጠው? እግዚኦ! እንላላንየጥያቄዎች አይነትና ብዛት በአእምሯችን ሲተራመስብንእናም ምሥጢራቱ ላይ ለመድረስ፤ ውስብስቡን ለመፍታት፤ዴርቶጋዳን ገፅ በገፅ እያጣፋን እንነጉዳለን

ሣይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ህያው ነው

ከዴርቶጋዳ ረቂቅና አስገራሚ ገፀ ባህሪያት አንዱሣይንቲስት ኢንጂነር / ሻጊዝ እጅጉ ነው።  ይህ ሰውአሜሪካንን የህዋው ልዕለ ሃያል ካደረጓት ሳይንቲስቶችአንዱ ነው። ሻጊዝ የኢትዮጵያ ልጅ ነው።እነሆ ሳይንቲስቱፊቱን ወደ እናት ሀገሩ መልሷልይለናል ዴርቶጋዳ። መላእውቀቱን፤ ንብረቱንና እሱነቱን ለሀገሩ መስጠት ከጀመረዓመታት ተቆጥረዋልሳይንቲስቱ ፊቱን ወደ ድሃ ሀገሩመመለሱ ደግሞ የተለያዩ መንግሥታትን ከፍተኛ ሽብርውስጥ ጥሏቸዋል። ሻጊዝ ከአሜሪካን መዳፍ እንዳይወጣየአሜሪካን መንግሥት ለሲ አይ ጥብቅ ትዕዛዝአስተላልፏል

ሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ የዓለማችንን ራዳሮች ሳተላይቶችናየመገናኛ አውታሮች በፈለገው ጊዜ መዝጋት የሚችልአእምሮ ያለው ነው።እና ይህ ሰው ድሃ ሀገሩን ለማንሳትበመነሳቱ አሜሪካንና እስራኤል ተረብሸዋል። በአረብሀገራት የስለላ መዋቅራት ታፍኖ ሊወሰድ ይችላልስለሚሉም ርምጃ መውሰድ አለባቸው። የእስራኤሉ ሞሳድበእጁ ሊያስገባው መረቡን ዘርግቷል። የሩሲያው ቢምየሻጊዝን ማንነት የሚያውቅ በመሆኑ እንቅስቃሴውንእየተከታተለ ከነህይወቱ አፍኖ ሊወስደው መሰናዶውንአጠናቋል። ከሁሉም በላይ የሚገርመው ደግሞ የኢትዮጵያመንግሥት የስለላ ድርጅት ወኪሎች የሳይንቲስቱን ህይወትየሚቀጥፉበትን አመቺ ጊዜና ሰአት እየተጠባበቁመሆናቸው ነው። ”…ይህ ሰው እንኳንስ ጭንቅላቱናሊቅነቱ አስከሬኑ እንኳን ኢትዮጵያን አይረግጣትም” – ሲሉዝተዋል፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የላካቸው ገዳይ ሰላዮች።ለምን? ማለታችን ግድ ነው ይህንን ሲነግረን ዴርቶጋዳ።

በዘረኝነት ላይ የተገነባውና ዘረኝነት የተጠናወተውየህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በኢትዮጵያዊነት የማያምንበመሆኑ ሀገሪቱን በማፈራረስ ላይ ይገኛል፤ ኢትዮጵያበጥፋት ዘመን ውስጥ ትገኛለች፤ ከዚህ ጥፋትየሚያወጣትየኖህ መርከብያስፈልጋታል። ሳይንቲስትሻጊዝ እጅጉ ሀገሩን ከፍፁማዊ ጥፋት ለማዳንየኖህመርከብ ከሚገነቡላት አንዱ ነው። እና ህወሃትየኖህመርከብከመታነፁና ከማለቁ በፊት አናፂውን ሳይንቲስትሻጊዝን እና ባልደረቦቹን ማጥፋት አለበትኢንጂነርሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ተከቧል፤ በማንኛውም ሰዓትከከባቢዎች በአንዱ ህይወቱ ልትጠፋ ትችላለችሻጊዝእጅጉ ግን ራዕይ አለው፤ ለሀገሩ ብርሃን የሚፈነጥቅከድህነትና ከአምባገነኖች የሚያላቅቅ ራዕይ አለውመንገደኛ ነው ሻጊዝ፤ ሩቅ አላሚሩቅ ተጓዥእንቀንጭብ ከዴርቶጋዳ፤

“…ኢትዮጵያ መጪው ትውልድ ከፍሎ የማይጨርሰውብድር ተበድራለች። እያንዳንዱ ወጣት እያንዳንዱ ታዳጊየሚወርሰው ሌላ ነገር የለም።የገንዘብ ዕዳ፤ የሞራልዕዳ፤ የደም ዕዳ ኢትዮጵያውያን ነዳጃቸው ላይ ቆመውእየለመኑ ነው። ኢትዮጵያውያን ዩራኒየማቸው ላይ ቆመውነዳጅ አጥሯቸዋል።የኢትዮጵያ ጥቋቁር አልማዞች ጥቁርአልማዛቸው ላይ ቆመው እየተመፀወቱ ነውወንድሜሚራዥእኔና አንተስ እስከመቼ ዝምእንላለን?..እስከመቼ ድረስ ዳር እንቆማለን?” ሳይንቲስትሻጊዝ እጅጉ ለዶ/ ሚራዥ የተናገረው ያገጠጠ ሀቅሰውነታችንን እንደ ኤሌክትሪክ ንዝረት ሲወረውይሰማናል። ጥያቄው ለኛም መሆኑ ይከሰትልናልና።

ሻጊዝ የሚናገረው የእያንዳንዳችንን ዐይነ ውሃ እየተመለከተእንደሆነ ሁሉ ይሰማንናሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመነህወሃት ምዝበራዋና ፍዳዋ፤ ሰቆቃዋና የደም ዕዳዋ ገዝፎበጣዕር ድምፅ ስትጠራንና ዓይኖቿ የመከራ ዘመን ልጆቿንመድህንንት ለማግኘት ሲንከራተቱ ይታየንናበእስከዛሬውየምንቸገረኝምግባራችን ሀፍረቱ ያሸማቅቀናል። ስለምንእኛ ልንወጣው የሚገባንን ዕዳ ለመጪው ትውልድለልጆቻችን እናስተላልፍላቸዋለን? ስለምን ያለዕዳቸው ዕዳእንሰጣቸዋለን? ዝምታችን የሚያበቃውስ መች ይሆን? እስከመቼ በዚህ እንዘልቃለን?…እንላለን ለራሳችን፤ህሊናችን ሲወቅረን እየታወቀን

እንመለስ ወደ ዴርቶጋዳ ትረካ፤

እስከመቼ!” አለ ሚራዥ ውስጡ ተቃጥሎ። እኔ በበኩሌከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ማንኛውንም ተግባር ለመፈፀምዝግጁ ነኝ። ግን ምን ማድረግ እችላለሁ? የችግሩ ሰንሰለትተቆርጦ የማያልቅ ነው። የሰው ሀይልና በቂ ገንዘብያስፈልጋል።ይህ የሚራዥ ጭንቀት ቀልባችንንይስበዋል። ዕውነቱን ነው ሚራዥ እንላለን ምን ማድረግእንችላለን?”እናስተጋባለን እኛም የሚራዥን ጥያቄ።

ዕውነት አይደለም ይላል ሳይንቲስት ሻጊዝለሚራዥምለኛም። በቂ ገንዘብ ብቻ አይደለም የሚፈልገው። ብዙህዝብም አይደለም የሚፈልገው። ልብ ለልብ ከተገናኘንናአብረን ከሰራን እንኳንስ አንዲት ሀገር ዓለምን መለወጥየሚያስችል ዕውቀትና አቅም አለን…” ዕቅጩንይነግረናል ሻጊዝ፤ ለዶ/ ሚራዥ ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ለኛየሚመልስልን እስኪመስለን

“…ይልቅ እኔም አንተም ሞት ሳይቀድመን ወገኖቻችንንከሞት የምንታደግበት ወቅት ላይ ነን።ኢትዮጵያ ተስፋበቆረጡ ወጣቶች ተሞልታለች። ራዕይ ያጡ ህዝቦችጎተራ ሆናለች። ራዕይ የሌለው ህዝብ ደግሞ ይጠፋል።የተስፋው መስኮት መከፈት አለበት። ኢትዮጵያን ሌላሰው መጥቶ አይለውጥልህም። አንተን ለመለወጥ ሌላሰው አይመጣም። ይህን ሀቅ እወቅ። ኢትዮጵያ ውስጥ ብትን የሚሉት ቻይናዎችና አረቦች ሁሉ ለአንተብልፅግና ግድ የላቸውም። ሀገርህን ከቅጥረኞችናከወሮበሎች የምታድንበት ጊዜው አሁን ነው።

አንድ ጥያቄ እንድጠይቅህ ፍቀድልኝአለው ሚራዥ

ጠይቀኝ…”

ወደ ጦር ሜዳ እየላከኝ ነው?”

                                            *         *         *

ይህ የሻጊዝና የሚራዥ ምልልስ አንዳች ልዩ ስሜትንበውስጣችን ሲያቀጣጥል ይሰማናል። ተስፋ ይታየናል። ያምተስፋ የሚጀምረው ከራሳችን እንደሆን ስንገነዘብም በራስየመተማመን ስሜታችን ከውስጣችን ሲንር ሲንተገተግ፤ችቦው ሲለኮስ ይታወቀናል። ዕውነት ነው እንላለን፤ ራዕይየሌለው ትውልድ ተስፋ የለውም፤ ተስፋ ከሌለውበመንፈስም በምግባርም የጠወለገ ትውልድ ይሆናል፤የጠወለገ ትውልድ ደግሞ እያዘገመ ይሞታል። እና ጊዜውአሁን ነው እንላለን። ሀገራችን ማጥ ውስጥ የገባችውናእንዲህ ያለው አሳዛኝና አደገኛ ደረጃ ላይ የደረሰችው በኛውትውልድ ነው። ተስፋ በቆረጠና ራዕይ በራቀው ወጣትትውልድ ለመሞላቷ አንዱ ምክንያት እኛ በእድሜየሰነበትነው (1966 / አብዮት ፍንዳታና ማግስት ወስጥየተሳተፍነው/ባንሳተፍም የኖርነው) ትውልድ አካላት ነን፤አንድም በዝምታችን አንድም በጥፋት ተባባሪነታችን።

አዎ እውነት ነው! ኢትዮጵያን ሌላ ስው መጥቶአይለውጥልንም። ኢትዮጵያ በሀራጅ እየተሸጠች ነው፤ለቻይናው ለህንዱ ለአረቡ። ኢትዮጵያውያን በገዛ ሀገራቸውባይተዋርና ባርያ፤ በምርታቸው የበይ ተመልካች ሆነዋል።የደደቢቱ ህወሃት ክፉ አገዛዝ የኢትዮጵያን ለም መሬትየሚቸበችብላቸው ባዕዳን ሌት ተቀን የኢትዮጵያን አንጡራሀብት የሚጭኑት ወደ ሀገሮቻቸው እንጂ ለኢትዮጵያውያንዕድገትና ብልፅግና በሚውልበት መንገድና ስምሪትበኢትዮጵያ ምድር አይደለም። ዘርፎ ለዘራፊ በሯን በርግዶበከፈተው ወንጀለኛና ወሮበላ የህወሃትና ህወሃታውያንአገዛዝ አዝማችነት ዓለም አቀፍ የምዝበራ ቡድናትኢትዮጵያን በያቅጣጫው እየተቀራመቷት ናቸው። ማንከእኛ በቀር ሊያድናት ይችላል?…ከእኛስ በቀር ማን ህይወቱንገብሮ ኢትዮጵያን ሊታደጋት ይችላል?

እንቀጥል ቅኝታችንን፤

የሻጊዝ ራዕይ ወዴት ያመራ ይሆን? የሚራዥስተልዕኮ?…ዴርቶጋዳ ሴራውና ታሪኩ እንደ ሸረሪት ድርእየተወሳሰበና እየሰፋ፤ ከድርጊት ወደ ድርጊት ከምሥጢርወደ ላቀ ምሥጢር ሲወነጨፍ፤ ልባችንም አብሮእየተወነጨፈ ይነጉዳል

እንቀንጭብ ከትርክቱ ሂደት፤

እነሆ በጃንዋሪ 13 2006 ከኦስቲን ቴክሳስ ታላቅ የሀዘን ዜናበዓለማችን ህዋ ላይ ተናኘ፤ የሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ሞት።

ሳይንቲስቱ ፊቱን ወደ ድሃ ሀገሩ በመለሰና ሀገሩን ከጥፋትለመታደግ የፖለቲካ መዋቅር ባቆመ በሁለት ዓመት ውስጥ፤ኢትዮጵያዊው የህዋ ሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ በተወለደ 58 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷልአሉን አሜሪካኖቹ።እልል አለ የህወሃት/አህአዴግ  አገዛዝ፤ እፎይ ብሎ ተነፈሰ፤ሻጊዝን አድነው እንዲያጠፉለት የላካቸው ነፍሰ ገዳዮችበእጃቸው የሳይንቲስቱን እስትንፋስ እንዳቆሙለት ሁሉእየተሰማው። ይህ  እውነት ነው፤ ሻጊዝ ሞቷል።ግናሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ዕውን የሞተው ተፈጥሯዊ ሞትነውን?! ዴርቶጋዳ ስለሻጊዝ ሞትና ከሞት ወዲያ ባለውህያው ህይወቱ ቀልባችንን ሰድሮ፤ ሀዘናችንን አስውጦውስብስቡን ታሪክ እያፍታታያልተገለጠልንንእየገላለጠልን ትረካው ይንቆረቆራልምሥጢሩምይበራያል

                                       *       *      *

ሳይንቲስት ኢንጂነር / ሻጊዝ እጅጉ አልሞተም፤በዴርቶጋዳ፤ በዴር 33 በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ከርሰምድር፤ በምድረ ኢትዮጵያ፤ ዘላለማዊ ህያውነትንተቀዳጅቷል። እንዴት? ለእኒህና ለሌሎችም የዴርቶጋዳምሥጢራትዴርቶጋዳን ማንበብ ብቻ ይሆናልመፍትሄው። ቁንፅል ስዕላዊ ቅኝታችን ግና ይቀጥላል፤  

አባ ዠንበሩ በሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ውስጥ ህያውሆነዋል። ለኢትዮጵያ ክብር፤ ልዕልና እና ብልፅግና ህልምየነበራቸው። ነፃነቷን፤ ታሪኳንና ቅርሷን ጠብቀው ያቆዩንአባቶቻችን  ተምሳሌ ናቸው አባ ዠንበሩ። እና ሳይንቲስትሻጊዝ የአባ ዠንበሩን ህልም ዕውን አደረገና ሞተ።አባዠንበሩም ሞቱ፤ ህልማቸውና ራዕያቸው ግን አልሞተም።

አዎ ሳይንቲስት ሻጊዝ ሞቷል፤ ዓርማው ግን አልወደቀም።በዶ/ ሚራዥ፤ በሞሳዷ ሲራጳ፤ በአሜሪካ አየር ሀይልውስጥ ዝነኛ አብራሪ በነበረው ጌራ፤ በቁጥር ሁለትየዴርቶጋዳ ኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶችና ምሁራን፤ በዴር33 ራዕዩ ዛሬም አለ። እኒህ ሁሉና በዚህ ቅኝት ያላነሳናቸው የዴርቶጋዳ ገፀ ባህርያት  በታሪኩ ውስጥ ባላቸው ሚና እናሰብዕና ዕውቀትና ተልዕኮ አንባቢን በስሜት ማዕበልእያናጡ፤ በታሪኩ መርከብ እያንሳፈፉ፤ ከምዕራፍ ምዕራፍእሚያስፈነጠሩ ናቸው

ዴር 33 በሳይንቲስት ሻጊዝ የተነደፈች በዴርቶጋዳጥበበኞች ህልውና ያገኘች፤ እንደ መኪና በየብስ እንደአሞራ በሰማይ የምትበር የተራቀቀች የዴርቶጋዳ ውጤትናት። ዴር 33 የዴርቶጋዳ አባላት ራዕይ ተምሳሌ ናት። ዴር 33 የሳይንስ ልቦለድ ናት አትበሉ። ሻጊዝ እጅጉ ዛሬ ዓለምየሚገለገልበትን ኤስ (አቅጣጫ አመልካች) አልፈለሰፈምን? ታዲያ ዴር 33 እንደምን የሳይንስ ልቦለድብቻ ልትሆን ትችላለች? ዴር 33 ራዕያችን ናት፤ የአባዠንበሩ ራዕይ፤ የሻጊዝ ራይዕ፤ የኢትዮጵያ ወጣትትውልድ ራዕይ

ይልቅስ ለዚህች ልዩ የዚህ ትውልድ ራዕይ 33 ቁጥር ለምንመታወቂያዋ ሆነ? አዎ! ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅከዘመናት የዲያቢሎስ ባርነት ነፃ ሊያወጣ ከሀጢያቱምሊያነፃው ራሱን አሳልፎ በመስቀል ተቸንክሮ የሞተው 33 ዓመቱ ነበር።እና የዴር 33 ተምሳሌነት ይህ ወጣትትውልድ የሀገሩ መድህን፤ የሀገሩ ትንሳኤ፤ የሀገሩ ራዕይሆኖ ሀገሩን ይታደጋት ወገኑኑም ከናዚስት ህወሃትባርነት ነፃ ያወጣ ዘንዳአመልካች ትሆን? ማለታችንግን አልቀረም።

ልጅ በአባቱ ሀጢያት አይኖርም

አባ ፊንሐስ ወንጀለኛ ናቸው። አባ ፊንሐስ ከሀገራቸውብሶትና ሰቆቃ ይልቅ ግላዊ ህይወታቸው የሚደላደልበትንናየሚከብሩበትን ህልም ሲያልሙ  – ለዚህም ደፋ ቀና ሲሉየኖሩ አባት ናቸው። አባ ፊንሐስ መንፈሳዊ አባትነታቸውለአለማዊ ህይወታቸው ካባ ሆኖ የሸፈነላቸው አባትናቸው።እንዲህ ያሉ አባ ፊንሐሶች በየትውልዱ ሁሉተፈጥረዋል፤ ነበሩም። ዛሬም ናዚስት ህወሃትን አገልጋዮችብዙ አባ ፊንሐሶች ሞልተዋልየዴርቶጋዳው አባ ፊንሐስለኒህ ሁሉ ተምሳሌያዊ ገፀ ባህሪ ናቸው።

አባ ዲዲሞስ ሩቅ ተጓዥ ራዕይ የነበራቸው አባት ነበሩ።አባ ዲዲሞስ አዋቂ ናቸው፤ የተማሩ። የአባ ዲዲሞስራዕይና ዕውቀት ግና በሥልጣን አባዜ ተሸበበ፤ ታወረ።አቡነ ጵጥሮስን የተቃወሙትም ለዚሁ ነበርሥልጣንንበእሳቸው በኩል ማግኘት ከመቻላቸው በፊት ስለሞቱ። እናአባ ዲዲሞስ ዕውቀታቸውንና ሩቅ ተጓዥ ራዕያቸውንለሥልጣን አባዜ የሸጡ አባቶቻችን ሁሉ ተምሳሌ ናቸው።በየትውልዱ ብዙ አባ ዲዲሞሶች ተፈጥረው አልፈዋል፤ዛሬም በዚህ ትውልድ ውስጥ የናዚስት ህወሃት አገልጋይየሆኑ አያሌ አባ ዲዲሞስ ምሁራንም ተናኝተው ይገኛሉ

የሞሳዷ ሲጳራ የአባ ፊንሐስ ልጅ ናት። ሲጳራ ግን በአባቷወንጀል አልኖረችም። ጌራ እና ሞረዳ የአባ ዠንበሩን ራዕይአንግበዋል። ሚራዥ በአባቱ ፈለግ ተተክቷል።  ሁሉምየሳይንቲስት ሻጊዝን አርማ አንስተዋል። ነገ ሌላ ቀን ነው፤ነገ በኢትዮጵያ አዲስ ቀን ይወጣል

እኒህ ምርጥ ወጣቶች በዴርቶጋዳ የምናገኛቸው የዚህትውልድ ተምሳሌት ናቸው። እኒህ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ገንቢወጣቶች በአባቶቻቸው ሀጢያት አይኖሩም። በአባቶቻቸውራዕይ እንጂ!! ኢትዮጵያን ዛሬ ናዚስት ህወሃትና በ አምሳሉ የፈጠራቸው ህወሃታውያን ከከተቷ  መቀመቅየሚያወጣትም ይህ ወጣት ትውልድ ነው። ይነሳል ክንዱንአጠንክሮ፤ በኢትዮጵያዊነቱ ተባብሮ! ያውለበልባልአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራውን ከፍ አርጎ! ይዘምራልበህብረ ድምፅ፤ ከአድማስ አድማስ ያስተጋባልይላል ኦርያኢትዮጵያ!…ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝ!!

መሸበቢያ

ክብር የእግዚአብሄር ነው። ምሥጋናም በእግዚአብሄርይሰምራል። አስጀምሮ ላስጨረሰኝ ዴርቶጋዳለብላቴናውይስማዕከ ወርቁክብር ምሥጋናዬ በላይኛው ፈጣሪ ስምባለህበት ይድረስህ። በነገይቷ ኢትዮጵያ መፃዒ ዕድልበወጣቱ ትውልድ ራዕይ ተስፋ ሰጥተኸናልናፀሎታችንእውን ይሆን ዘንድ እንማልዳለን።

እነሆ ተስፋችንን በዴርቶጋዳ ከውስጣችንእንደቀሰቀስከው፤ የላይኛው መልዕክተኛ መልዐክምበውድቅት ሌሊት፤ በድቅድቅ ጨለማ ከተኛህበት መጥቶደግሞ ደጋግሞ ይቀስቅስህ። ከራስጌህም ቆሞ መለኮታዊብርሃኑን ያብራልህ። ከክንፉም ላባ ነቅሎ፤ እንደ ብዕርምቀርፆ በእጅህ ያስጨብጥህ። መለኮታዊ የኢትዮጵያ ትንሳዔመልዕክቱም በመላዕክት ልሳን ይገለጥልህ። በብራናህምትከትበው ዘንዳተስፋ ላጣው ለተስፋይቱ ምድር ህዝብተስፋ ትናኝም ተስፋም ታዳርስ ዘንዳ ደግመህ ደጋግመህፃፍ። ዛሬም ነገም ለዘለዓለሙአሜን!

 ሰኔ 2010 ዓ/ም (ጁን 2018)

ሲድኒ አውስትራሊያ

mmtessema@gmail.com

ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ የሚገኝበትን ሁኔታ የሚያሳዩ ዋቢ ቪዲዮዎች

https://www.youtube.com/watch?v=Hlt17elS844

https://www.youtube.com/watch?v=hMcPk9c0Ajo&t=92s

https://www.youtube.com/watch?v=Wl3KhASzpB0&feature=youtu.be

LEAVE A REPLY