ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

 ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም.

ለ፦ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
    የኢትጵያ ፌዴራል ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስቴር
    አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

ከ፦ ፍትህ ለኢትዮጵያ ግብረኃይል
    2201 Murfreesboro Pike, Suite A-109
Nashville, TN  37217

ክቡር ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ፤

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴርነትን ከተረከቡበት ጊዜ አንስቶበኢትዮጵያችን የፈነጠቀው የዴሞክራሲ የአንድነት የነጻነትናየፍቅር ተስፋ ለምልሞ ፍሬ አፍርቶ ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞገናናነቷ እንደምትመለስ ለሚወድዎት ሕዝብ አብስረዋል፡፡ለዚህ ለተቀደሰ ታላቅ ግብ አቅም በፈቀደ ሁሉ ከጎንዎበመቆም ኢትዮጵያዊ ሃላፊነታችንን እንደምንወጣ እናረጋግጥልዎታለን፡፡

በሀገራችን ቂምና ቁርሾ ቀርቶ አንድነት፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲጎለብት በተለያዩ ጊዜ የሚወዱትንሕዝብ ተማጽነዋል፡፡ ይህ ማለት ግን ወንጀል ሲሰራ አይቶ ፊትንማዞር ወይንም አንድ ወንጀል የሰራ ሰው ደግሞ የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት በፍ/ቤት ተጠያቂ እንዳይሆን ወይምበበዳይና በተበዳይ መካከል እርቅ ሳይወርድ ወንጀሉ ተዳፍኖይቅር ማለትዎ እንዳልሆነ መገመት የቻላል፡፡ ክቡርነትዎ እንደሚታወቀው የአፄ ኃይለሥላሴ ዘውዳዊ መንግስት በሕዝባዊ አብዮት ከተወገደ በኋላ እጅግ ጨካኝና አምባገነናዊ ወታደራዊ መንግስት በትረ–ስልጣኑን ጨብጦ ለአስራ ሰባትዓመታት ሕዝብን በተለይም ወጣቱን ጭዳ እያደረገሲጨፈጭፍ ሃይ ያለው አልነበረም፡፡

ሃገራችን በተለይም አዲስአበባ በወጣት የደም ጎርፍ ታጥባለች፡፡ በገጠሩ ወጣቶችበየመንገዱ ተገድለው ተጥለው የጅብ እራት ሆነዋል፡፡ በአምኒስቲ ኢንተርናሽናል ስሌት መሰረት በመንግስቱኃይለማርያም መንግሥት ትእዛዝ 500,000 ኢትዮጵያውያንተጨፈጭፈዋል። ቀይ ሽብር ተብሎ በተሰየመው ትውልድየማጥፋት ዘመቻ አባቱ ወይም እናቱ ወይም እህቱ ወይምወንድሙ ወይም ልጁ በሞት ያልተቀጠፈ ቤተሰብ የለም ማለትያስቸግራል፡፡ ይህ መዓት ከወረደ እጅግም ሩቅ ባለመሆኑ ዛሬምወላጅ አልባ የሆኑ ወጣቶች እና ጠዋሪ አልባ የሆኑ አዛውንትበሃዘን ተቆራምተው ያነባሉ፡፡

በ 1983 ዓ.ም የኮሎኔል መንግስቱ አስተዳደር በኢትዮጵያ ሕዝብአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በጦር ሃይልከተወገደ በኋላ ኢሕአዴግ በትረ ስልጣኑን በጨበጠ ማግስትኮሎኔል መንግስቱ ወደ ዝምባብዌ ሲፈረጥጥ የተቀሩት የደርግአባላት ወህኒ ወርደዋል፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ በፌደራልከፍተኛው ፍርድ ቤት መንግስቱን (በሌለበት) ጨምሮ የወንጀልክስ ተመስርቶባቸው ፍ/ቤት ቀርበዋል፡፡ የቀረበባቸውም የክስመስመር የጦር ወንጀል ሆኖ፤ ሲዘረዘር የዘር ማጥፋት ወንጀል(genocide)፤  በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል (crime against humanity)፤ ሰቆቃ (torture)፤ ሌሎችም፤ ሲሆኑ በቀረበባቸው ክስጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ ጠበቃ ቆሞላቸው እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡ የደርግ አባላቱ በሙሉ፤ መንግስቱ ኃይለማርያም ደግሞ በሌለበት ጥፋተኛ ተብለው በአብዛኛዎቹ ላይ የሞትቅጣት ተበይኖባቸዋል፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫሕግ በሚደነግገው መሰረት የሞት ቅጣቱ ወደ እድሜ ልክእስራት ተቀይሮ፤ የእስራቱ ጊዜም በአመክሮ ተቀንሶ እጃቸውከተያዘ ከአስር ዓመት በኋላ ከእስር ተፈትተዋል፡፡ መንግስቱኃይለማርያም ክሱን ሳይከራከር የሞት ፍርድ ተፈርዶበት  ፍርዱወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮለት አንድም ቀን ሳይታሰርአሁንም ዝምባብዌ እየኖረ ለዓለም አቀፍ  መገናኛ ብዙሃንዝንብም አልገደልኩም፤ እያለ በግፍ በተጨፈጨፉት ንጹህኢትዮጵያውያን ላይ ያፌዛል፤ ያላግጣል፡፡ በመሆኑም እስከ ዛሬበመንግስቱ ኃይለማርያም ላይ ሕግ የሚፈቅደው ምንምእርምጃ አለመወሰዱ ኢሕአዴግ ለፍትህ ያለውን ግዴለሽነትያመለክታል፡፡

ክቡርነትዎ በተደጋጋሚ በሀገራችን ፍትህ እንዲሰፍን ያላሰለሰጥረት እንደሚያደርጉ ቃል የገቡ ሲሆን የኮኔሌል መንግስቱየፍርድ ውሳኔ እንዲፈጸም ማድረግ የዚሁ ቃል አካል ነው፡፡

ስለሆነም በ “ፍትህ ለኢትዮጵያ ግብረኃይል” አመለካከት ለፍትህሲባልና ለወደፊቱ በኢትዮጵያ መሪዎች ተመሳሳይ ወንጀልእንዳይደገም ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መፍትሄዎች አንዱይተገበር ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

• ከዚምባብዌ መንግስት ጋር በመደራደር ኮኔሌል መንግስቱወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ የፍርድ ውሳኔ እንዲፈጸምበት ማድረግ፡፡
• የቻዱ ፕሬዘዳንት ሁሴን ሀብሬ የሃገሩ የቻድ ፕሬዘዳንት በነበሩበት ወቅት ለፈጸሙዋቸው ወንጀሎች ጎረቤትበሆነው በሴኔጋል የተባበሩት መንግስትና የሴኔጋልመንግስት ትብብር ባቋቋሙት ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸውእንደተፈረደባቸው ሁሉ መንግስቱም በተመሳሳይ መልኩበአንድ በጎረቤት ሃገር ክስ እንዲቀርብበት በአክብሮትስናሳስብ አላማችን ቂም በመቋጠር በቀል ለመወጣትሳይሆን በአገራችን ፍትህ እንዲሰፍን ማንም ሰው ለሰራውወንጀል የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት ተጠያቂ እንዲሆንበአክብሮት ለማሳሰብ ብቻ ነው፡፡

ከታላቅ አክብሮትና አድናቆት ጋር፤
ፍትህ ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል

___________________________________________

ሊቀመንበር – አምባሳዶር እምሩ ዘለቀ

የቦርድ አባላት፤    


አቶ ኪዳኔ አለማየሁ፤

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤

ዶ/ር ምስማኩ አሥራት፤  

አቶ ተስፋሚካኤል መኮንን፤

አቶ ፀሐይ ደመቀ፤

አቶ ነሲቡ ስብሐት

ግልባጭ፤


ለኢትዮጵያ ኤምባሲ

3506 International Drive, NW

Washington, DC 20008, USA

ለኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ሚስዮን

866 2nd Ave #3,

New York, NY 10017, USA

ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

P.O.Box 393

Addis Ababa, Ethiopia

LEAVE A REPLY