ሀለሐመ /በገጣሚ ማህሙድ እንድሪስ/

ሀለሐመ /በገጣሚ ማህሙድ እንድሪስ/

ሀለሐመ
ሀለሐመ
የሚል ግጥም የገጠመ
ትልቅ ክብር
ትልቅ ሹመት
ትልቅ ህንጻ ተሸለመ ።
እኔም በዚህ ተወስውሼ
አልኩና ከማን አንሼ
ብየ ገጠምኩ
ሠረሰሸ
ሠረሰሸ
ሠረሰሸ
ሠረሰሸ
ሆኖም ያቅሜን በመጻፌ
እንኳን ልሞገስ ልሸለም ተሰድቤ ተወቅሼ
“ያገር ሰላም በማደፍረስ” በሚል አንቀፅ ተከስሼ
ይህን “ወንጄል” እንዳልደግመው አስጠንቅቀውኝ ስወጣ
ሌላው የዋህ የኔ ቢጤ
ከ— ሠረሰሸም አለፈና
ቀበተቸ
ቀበተቸ
የሚል ግጥም ይዞ መጣ
ተመልከቱልኝ ይህን ሰው
እሞገስ እሸለም ብሎ ሲወርድበት መአት ጣጣ
በሽብር ወንጄል ተከሶ
አስራ አምስት አመት ተቀጣ ።
ነጻ ወጣን ባልን ማግስት
ባልተጻፈው ህገ መንግስት
ከተፈቀደልህ ክልል ውጭ አልፎ መሄድ ያስጠይቃል
አገራዊም ኪነ ጥበብ ግጥምም ይሁን ስነ ቃል
ሀለሐመ ላይ ጄምሮ ሀለሐመ ላይ ያበቃል ።

LEAVE A REPLY