በመጥፎነቱ የሚታወቀው በረከት ስምኦን እና ታደሰ ጥንቅሹ ታሰሩ

በመጥፎነቱ የሚታወቀው በረከት ስምኦን እና ታደሰ ጥንቅሹ ታሰሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ – ባለፉት እስርት አመታት ኢህአዴግን በመዘወርና የመለስ ዜናዊ ቀኝ እንደነበር የሚታወቀው በረከት ስምኦን በቁጥጥር ሰረ መዋሉ ታወቀ።

በጃፓን ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው የመኖሪያ ቤቱ መያዙ የታወቀው በረከት ስምኦን ባልደረባው ታደሰ ካሳም (ጥንቅሹ) አብሮ በቁጥጥር ስር መዋሉ ለማወቅ ተችሏል።

አቶ ታደሰ ጥንቅሹ (ካሳ) እና አቶ በረከት ጥረት በመባል የሚታወቀውን ድርጅት ለረጅም ጊዜ በመምራት የሚታወቁ ሲሆን በድርጅቱ በፈጸሙት የስርቆትና የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው መያዛቸው ተገልጿል።

በረከት ስምኦን በመጥፎነቱ ከሚታወቀው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ውስጥ በሰው ልጆች ላይ ይደርስ የነበረ የሰብአዊ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውሶች ዋነኛ ተጠያቂ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።

LEAVE A REPLY