ዶ/ር አብይ ከተፎካካሪ ድርጅቶች አመራር  ጋር ዛሬ ውይይት ላይ  ናቸው

ዶ/ር አብይ ከተፎካካሪ ድርጅቶች አመራር  ጋር ዛሬ ውይይት ላይ  ናቸው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ዶ/ር አብይ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች  ጋር ዛሬ ውይይት ላይ  መሆናቸው ተገለጸ።

አራት የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችም በውይይቱ ለየ ወረቀት እንደሚያቀርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ይፋ አድርጓል።

7C85B2C3-C02A-4F04-B48C-663297A282E6

ይህ ታሪካዊና በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክና ትርክት አይነተኛ የውይይት መድረክ ነው ያለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ውይይቱ ከጥቂት ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋባዥነት ከተደረገው መድረክ የቀጠለ ነው ብሏል።

የዛሬው ውይይት አስተባባሪ አንዱ የሆኑትን የሺዋስ አሰፋ (ሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር) እንደተናገሩት የመድረኩ ዋና አላማ በዚህ የፖለቲካው ሽግግር ወቅት የፖለቲካ አመለካከትን በሰላማዊ መንንገድ የመለዋወጥ ልምድን ለማሰደግ ነው። ማለታቸውን ጽህፍት ቤቱ ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትላንት በፓርላማ ለቀረበላቸው ጥያቄዎች በተለይ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በሚመለከት በሰጡት ጠንካራ መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY