“ጃ ያስተሰርያል!” ቁጥር ሁለት || በላይ በቀለ ወያ

“ጃ ያስተሰርያል!” ቁጥር ሁለት || በላይ በቀለ ወያ

ወያኔነታቸው ከዚህ ሰረገላ
ስልጣን ሀክ ተደርገው ፣ ሲተኩ በሌላ
በአፈሙዞች ራስ ፣ ያስወጣችው ጠብሳ
ጋብዛ አስገባችው ፣ መቀሌ ላይ ምሳ
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
አስራ ሰባት መርፌው ፣ ወጋግቶን ሲወጣ
አስራ ሰባት ባንኮች ፣ የሚዘርፈው መጣ
ይህን ሁሉ እያየ ፣ ከአፉ ቃል ያልወጣ
አንዲት ቅኔ ብዘርፍ ፣ ቆይ ለምን ተቆጣ?
ይቅር በለውና ፣ ከፋፋዩን ወቅሰህ
አንድ የነበረን ህዝብ ፣ አንድ አርገው መልሰህ
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ኢትዮጵያ
እማማ አቢሲኒያ
ኢትዮጵያ ስሚ
እማማ አቢሲኒያ
ቂም በቀል ክፉ ነው ፣ከአምላክ ያለያያል
በቀለን በማሰር ፣ የህዋት ፅድቅ ይታያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ዘፅአት በኢትዮጵያ ፣ ወደ ለውጥ ጉዞ
ኩሬውን ሚያሻግር፣ ባህር ሀሳብ ይዞ
ቅርብ ነው አይርቅ ፣ የኢትዮጵያ ቀን መውጫ
ባንድነት ከጣልን ፣ ዱላ ክላሽ ሜንጫ
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ፍቅር አጥተን እንጂ ፣ በርሀብ የተቀጣን
ጭማሪ ጥላቻ ፣ ሚሰጠን መች አጣን
ኦሲሳ ኦሲሳ ፣ ኦሲሳ ማንደላው
ይቅርታን አያውቅም ፣ ክላሽ እና ዱላው
በተስፋዋ መሬት ፣ እንዲፈፀም ቃሉ
መሥጅት ቤተስኪያኑን ፣ አትናዱ አታቃጥሉ
እማማ ኤሎሔ አላሔ
እማማ አትሰማኝ ወይ በይው
እማማ ማማዬ እማማ
ይሔም በክፉ ቃል ፣ ይሄንን ሲወቅሰው
ይህም በጥላቻ ፣ ይሄንን ሲከሰው
ህዝቦች እመሐል ቤት ፣ የምንቧቀሰው
መለየት አቅቶን ነው ፣ ሚበጀውን ሰው
ኦኦኦኦ ያስተሰርያል

ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ያስተሰርያል
ጃ ማለት ፈጣሪ ፣ መሰረይ ይቅርታ
እኛ ሳንስማማ ፣ እንዴት ይስማን ጌታ
ኤሎሔ አላሔ
እማማ ማማዬ እማማ
እስቲ ተደመሩ ፣ እርስ በእርሳችሁ
እናንተን እያየ ፣ ህዝብ ይማርባችሁ
አንድ ሀገር አድኑ ፣ በልዩነታችሁ
አለበለዚያማ
በምን ያስታውቃል ፣ እኛን መውደዳችሁ?
።።።
አቤት ስቃይ ፣ አቤት ጠኔ
ኡንዱ ኬኛ ፣ ሁሉ የኔ
አልቅሰን ሳናባራ ፣ በወያኔ
እዚ ደግሞ ፣ ሌላ ትኩሳት
ሳይጠሩት አቤት ፣ ብሎ መነሳት
ወዲህ አፈናቃይ ፣ ወዲያ እድሳት
ወገኔ አለቀ ፣ በዘረኛ እሳት
እሳት
እሳት
እሳት
ኧረ አይነጋም ወይ
ኧረ አይነጋም ወይ ኢትዮጵያዬ

ቁጥር አንዱን ለትውስታ ልጋብዝዎ!

LEAVE A REPLY