“አረ የመንግስት ያለህ..!!!”፣የኢትዮጵያዊያን ጥሪ ከቻይና || ታምሩ ገዳ

“አረ የመንግስት ያለህ..!!!”፣የኢትዮጵያዊያን ጥሪ ከቻይና || ታምሩ ገዳ

ወጣት ሶሊያና አረጋዊ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የእድሜ አቻዎቿ ህይወቷን በትምህርት ለመቀየር እራሷን ቤተሰቦቿን እና አገሯንም ለመጥቀም ወደ ምድር ቻይና፣ ጓንጉ ግዛት ከተጓዙ ሶስት መቶ የሚጠጉ ተማሪዎች መካከል አንዷ ነች።

ባለፈው ጥር /ጀነዋሪ 7 2020,እኤአ ይፋ የሆነው እና የበሽታው መከሰትን ለመጀመሪያ ጊዜ የጠቆመው የሰላሳ እስራት አመቱ ቻይናዊ ዶ/ር ሊይ ዋንበርግን ጨምሮ ከሰባት መቶ ሀያ አራት በለይ ሰዎችን የገደለው እና ከሰላስ አራት ሺህ በላይ ሰዎችን ያጠቃው የኮሮና ቫይረስ የተከሰተባት እና ወደ አስራ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎቿ የአገር ውስጥ ሆነ አለማቀፋዊ እንቅስቃሴያቸው ከተገታው ዉሃን ግዛት ውስጥ የምትኖረው ሶሊያና ሰሞኑን በወዳጆች መረቧ (ትዊተር) ገጿ ላይ የምትለጥፋቸው የተለያዩ ወቅታዊ መልእክቶች ከኤርትራ፣ ጋና፣ ደ/አፍሪካ፣ ጋቦን፣ ምርኮ… ወዘተ የመጡ አምስት ሺህ የሚደርሱ እርሷን መሰል አፍሪካዊ ተማሪዎች በእየእለቱ ከስጋት፣ከጭንቀት እና ከሞት ጋር ሰለሚያደርጉት ግብግብ ያሳያል።

በምጣኔ ሀብት (ኢኮኖሚክስ) ትምህርት የአራተኛ አመት ተማሪ የሆነችው ሶሊያና ባለፈው የካቲት / ፌበርዋሪ 5,2020 እኤአ በለጠፈችው የትዊትፕር መልእክት ላይ” በቤጁንግ የሚገኘው፣እኛን የሚወክለው ኢምባሲ ለጥያቄያችን መቼ ይሆን ምላሽ የሚሰጠን?፣ በቾንግኪንግ ግዛት ከሚገኘው ተወካይ ከተላከልን ሁለት መልእክቶች በቀር እስከ አሁን ድረስ ለጥያቄያችን ምንም አይነት ምላሽ አልተሰጠንም። ለምላሽ ፍለጋ አጥብቆ መጠየቅ ተገቢ አይደለም ይሆን!”ስትል ጭንቀት እና ቅሬታ አዘል መልእክቷን አቅርባለች።

ከአምስት ቀናት በፊት ሶሊያናን ያነጋገራት ራዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል በበኩሉ እንደዘገበው የኢትዮጵያ መንግስት በዉሃን ግዛት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች እጣ ፈንታ ዙሪያ ለስብሰባ ሳይቀመጥ እንዳልቀረ ገልጿል።

ምንም እንኳን የሶሊያና እና መሰል ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ጩኸታቸው እና ጭንቀታቸው ተገቢውን መንግስታዊ ምላሽ አግኝቶ ሰለመሆኑ፣ ብዙውን ጊዜ ምስጢራዊነትን እና ሕዝቡን ስርፕራይዝ ማድረግ የሚያበዛው የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በምስጢር ይዞት ስለመሆኑ በውል ባይታወቅም ሶሊያና ቅደም ሲል እኤእ በየካቲት/ፌበርዋሪ 5/2020 ቤጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የጻፈችው “አረ አስታውሱን፣ አትርሱን” የትዊተር ጥሪዋ በሁኔታዎች መለወጥ (እንደ አንዳንድ አገራት ዜጎች የውሃን ግዛትን ለቃ ለመውጣት እድሉ ገጥሟት ይሁን)፣ በጫናዎች ሳቢያ ባይታወቅም “በዚህ ቀውጢ ወቅት በውሃን ግዛት የሚገኙ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር የበኩሉን እገዛ እያደረገልን ነው” ከሚለው መልእክቷ በቀር የትዊተር ድረሱልን መልእክቷ ከሁለት ቀናት ቆይታ በሁዋላ፣ አርብ እለት ከገጿ ላይ ተነስቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አገራቸው አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገው በረራውን ለጊዜው ገታ እንዲያደርግ ባለፈው ሐሙስ የተማጽኖ ጥሪ ያቀራቡት የጎረቤት ኬንያ ፕ/ት ኡሁሩ ኬኒያታ በዉሃን ግዛት በትምህርት ላይ ያሚገኙ ሰማኒያ ስምንት ኬኒያዊያን ተማሪዎች ባቀረቡት “የድረሱልን ጥሪ” መሰረት ተማሪዎቹ ወደ አገር ቤት መጥተው ቫይረሱ በውስጣቸው ስለመኖሩ እና ያለመኖሩ እስኪጣራ ድረስ ለአስራ አራት ቀናት በማቆያ ስፍራ ለመቆየት ከተስማሙ የናይሮቢ መንግስት ወደ አገር ቤት እንደሚያጓጉዛቸው መግለጻቸውን የደቡብ ቻይናው ሞርኒንግ ፖስት ጋዜጣ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት ምንም እንኳን በዉሃን ግዛት በአጣብቂኝ ውስጥ ሰላሚገኙት ከሶስት መቶ በላይ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ጉዳይ እስከ አሁን ድረስ ያለው ነገር ባይኖርም ከዉሃን ግዛት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ተጓዦች በሙሉ ለተወሰኑ ቀናት በማቆያ ስፍራዎች እንደሚያቆያቸው እና ተገቢው ክትትል እንደሚያደርግባቸው አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ ወደ አምስት የቻይና ከተሞች የሚያደርገው የዚህ ወር በረራውን ለጊዜው በ33% መቀነሱን ኳርቴዝ ጋዜጣ ዛሬ አስነብቧል።

LEAVE A REPLY