ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፌደራልም ሆነ የክልል ምርጫን ማካሄድ የሚያስችል ብቸኛ ሥልጣን ያለው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ አስታወቁ፡፡
የቀድሞ የነፃነት ታጋይና አሁን ላይ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ፤ ህዝበ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ትናንት ” ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ተዘጋጅቻለሁ” ሲል መግላጫ ማውጣቱን ተከትሎ ነው ሰብሳቢዋ የትኛውም የሀገሪቱ ክልል ምርጫ የማካሄድ ሥልጣን ያለው ተቋማቸው እንደሆነ አስረግጠው የተናገሩት፡፡
ክልላዊ ምርጫ ከጠቅላላ ምርጫ መርሀ ግብር ውጭ ማካሄድ የሚቻልበት አጋጣሚ መኖሩን ያመላከቱት ወ/ሪት ብርቱካን፤ ህወሓት ምርጫ ለማካሄድ ያለውን ፍላጎት ለቦርዱ አለማሳወቁን ጭምር ይፋ አድርገዋል፡፡
“ህወሓት ከዚህ ውጭ ምርጫ ቢያካሂድ ፍፁም ህጋዊነት የሌለው ነገር ነው፤ ያ ደግሞ ከኛ ሓላፊነት ውጭ ነው” ሲሉም ድርጅቱ ያወጣውን መግላጫ ውድቅ አድርገዋል።