ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ 5 ሺኅ 500 ሰዎች የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ (129) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተነገረ።
ይህን ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1 ሺኅ 934 መድረሱ ታውቋል።
ዛሬ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች 75 ወንድ እና 54 ሴት ሲሆኑ፣ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል ያለው የጤና ሚኒስቴር መግለጫ፤ በዜግነት ረገድ 124ቱ ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ የተቀሩት የደቡብ አፍሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ የአሜሪካ፣ የኤርትራ እና ሱዳን ዜጎች እንደሆኑም አብራርቷል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው 129 ሰዎች መካከል፤ 101 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 10 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 6 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 5 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 1 ሰው ከሐረሪ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል መሆናቸውን ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስታውቋል።

























