‹‹የኦሮሞ ትግል›› በሚል ካባ የተጠቀለለው የቄሮ የዘር ማጥፋት እና ዘረፋ አሰቃቂ የሽብር እንቅስቃሴ እንደሃረግ ተክል ራሱን ችሎ መቆም የማይችል ይልቁንም አጠገቡ ያገኘው ነገር ላይ መለጠፍና መጠምጠም የሚቀናው የነብሰ ገዳይ መንጋ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይሄ የሽብር ቡድን ሰበብ እንጅ ዓላማ የለውም፡፡ ለምሳሌ ሰሞኑን በሀጫሉ ግድያ አሳቦ ከ166 በላይ ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፏል፣ በብዙ መቶ ሚሊየን የሚገመት ንብረት ዘርፏል አቃጥሏል፡፡
ከዚህ በፊት ጃዋር ተከበብኩ ስላለ ብቻ በተመሳሳይ ከሰማኒያ በላይ ንፁሃንን ጨፍጭፏል፡፡ ከዛም በፊት ሰበብ አስባብ እየፈለገ ኦሮሞ ያልሆኑና ኦሮሞ ሁነው ይሄን እኩይ ተግባሩን ያልደገፉትን ሁሉ ሲገድል እና ሲያሰቃይ ነው የኖረው፡፡ ይሄ ቡድን ባህሪውን የወረሰው ከመሪዎቹ ሲሆን ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው አቋማቸው እንደ ሳሙና አረፋ የማይጨበጥ በአደገኛ የበታችነት ስሜት የተጠቁ ግለሰቦች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ትንሽ ሰበብ ፈልገው መንጋውን ለግድያና ዘረፋ ያሰማራሉ፤ በዚህም ተፈሪነትንና የፖለቲካ የበላይነትን ለማግኘት ይጥራሉ፡፡
ለምሳሌ ሰሞኑን የሚያደርጉትን አስቂኝም አሳፋሪም ነገር እንመልከት፤ አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ስቴቶች በሚደረጉት ሰልፎች በራሳችን ሰው ይሰማናል የሚል እምነት ስለሌላቸው የፈረንጅ አገር ጎዳና ላይ የወደቁ ሆምለሶች /የጎዳና ተዳዳሪዎችን / ሳይቀር የሲጋራ መግዣ እየሰጡ መፎክር ሲያስጮሁና ‹‹መላው ዓለም ከእኛ ጋር ቁሟል›› የሚል መልእክት ለማስተለለፍ ሲሞክሩ ነበር፡፡ አንዳንዶቹም አሜሪካ ተወልደው ያደጉ እንኳን ጥይት ፊኛ ሲፈነዳ የሚያለቅሱ ልጆቻቸውን ሰብስበው ይለቀስበት ይዘፈንበት በማያውቁት የኢትጲያ ጉዳይ ፅፈው የሰጧቸውን ተረት ሲያስነበንቧቸው ነበር፡፡ በሌላ በኩል ከሰሞኑ የተጧጧፈው የጥቁር አሜሪካዊያን ዘመቻ ጋር የእነሱን የበከተ አጀንዳ ይዘው ለመጠጋጋት ሲታገሉ እያየን ነው፡፡
ከላይ እንዳልኩት የቄሮ ሽብር ራሱን ችሎ መቆም አይችልም፡፡ ሁልጊዜ የሚንጠላጠልበት ምክንያት ይፈልጋል፡፡ በእርግጥ በፖሊስ እና በነጮች የበላይነት ለዘመናት በባርነት እና በቀለማቸው ምክንያት እየተመረጡ ግፍ እየተፈፀመባቸው ያሉ ጥቁር አሜሪካዊያን የገዛ ወገኑ ላይ አሰቃቂ የዘር ማፅዳትና ጭፍጨፋ ከሚፈፅም አቅመዳካሞችና ሴቶችን በመንጋ ጨፍጭፎ ከሚገድል ሰው ዘቅዝቆ ከሚሰቅል የእናቶችና አባቶችን ሬሳ በየመንገዱ ከሚጎትት ቡድን ጋር እንኳን ህብረት ማድረግ ከጎናቸውም ቁሞ ለመታየት ይጸየፋሉ፡፡ ምክንያቱም ቄሮ ገዳይና ዘራፊ ቡድን እንጅ የነፃነት ታጋይም ይሁን ህዝብ የሚወክል ዓላማ ያለው ቡድን አይደለም፡፡
የፈለገ ቢሸፋፈን የቄሮን ነብሰ ገዳይነት መሸፈን ተራራን በኪስ የመያዝ ያህል የማይቻል ነው፡፡ እዚህ ቡድን ጋር ማንም የሰው ዘር አብሮ አይቆምም፡፡ ዓለም ይህን እየተረዳ ነው፡፡ ገና ይረዳል፡፡ ለዛም ነው ቄሮና ደጋፊዎቹ እንደህፃን ልጅ የራሳቸውን አይን ሲጨፍኑ ከአለም የተደበቁ የሚመስላቸው፡፡ ራሳቸውን ማየት የማይችሉት ራሳቸው ብቻ ናቸው ዓለም እያያቸው ነው፡፡
ሌላው ቄሮ ካላቅሙ እየተንጠራራ ሊለጠፍበት የሚሞክረው ሙስሊሙን ማህበረሰብ ነው፡፡ ቄሮ ‹‹ሙስሊም ነኝ ›› ሊል ይዳዳዋል፡፡ እስልምና ሃይማኖትን ተጠግቶ በተለመደ እስስታዊ ባህሪው ሙስሊሙን ህብረተሰብ አጋሩ የሆነ ለማስመሰል እየተፍገመገመ ነው፡፡ ‹‹ትንሽ ቆሎ ይዞ ወደአሻሮ ጠጋ ›› እንዲሉ፡፡ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ባህሪና የቄሮ ባህሪ ብዙ ቢሊየን ማይልስ የተራራቀ ነው፡፡ እንዴት ለሚል ሩቅ ሳንሄድ የቅርቡን እናንሳ! ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› በሚል መቸም በማይረሳ የሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል… የሰላማዊ ትግልን ጥግ ለዓለም ያሳዩ ኩሩ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ከመመስከር አልፈን በትግላቸው ከእምነቱ ውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ሳይቀር ተማርኮ አብሯቸው ቁሟል …አብሯቸው ሲጮህ ኑሯል፡፡
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በግፈኞች እጃቸው በካቴና ታስሮ ሲጎተቱ ቅስማቸውን ለመስበርና ትግሉን ለማሽመድመድ ጆሮ ጭው የሚያደርግ ግፍ ሲፈፀምባቸው …ለኢድ ሶሏት ሊሰግዱ በተሰበሰቡበት ሳይቀር በፖሊስ ብትር እየተቀጠቀጡ ደማቸው ሲፈስና በየእስር ቤቱ ታጉረው ህክምና እንኳን ተከልክለው ሲሞቱ… መስጊዳቸው ውስጥ ሳይቀር ቦንብ ሲወረወርባቸው ዓለም በግልፅ ያየው በደል ተበድለው እንኳን እንደቄሮ ሰላማዊ ሰው አልጨፈጨፉም ….አገራቸውን አልካዱም፤ መላው ህዝባቸው ጋር በቃልም ይሁን በድርጊት አልተጋጩም እንደውም ለጁመዓ ሶላት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያስደመመ ነገር ነበር ያደረጉት …የአገራቸውን ባንዲራ በባሉን አድምቀው ግፈኛውን ስርዓት እንጅ ህዝባቸውንም ሆነ አገራቸውን እንደማይጠሉ ለዓለም አሳዩ!! በዚህም ጨቋኛቸውን ከህዝብ ለዩት፡፡
በጣም የቅርቡን የአባይን ጉዳይ እንመልከት… በአባይ ጉዳይ የአረቡም አለም ሆነ ሌሎች አለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋ በሚደረገው እልህ አስጨራሽ የዲፕሎማሲ ትግል ባንዲራዋን ከፍ አድርገው እየተፋለሙ ያሉት ወንድምና እህቶቻችን የሚበዙት ሙስሊሞች ናቸው፡፡ አዎ! ሙስሊም ወንድሞቻችን በየሚዲያው ለአገራቸው እየተፋለሙ ነው፡፡ አየህ እንደብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ብዙ ጥያቄ አላቸው፣ እንደአገር ከተለያዩ ስርዓቶች በእምነታቸው ብቻ የደረሰባቸው በደል ነበር፣ ወደኋላ ሂደው የመገፋት ታሪክ እያላዘኑ ከጠላት ጋር አልገጠሙም፤ ለአንዲት ሰከንድ በአገራቸው ጥቅም አልተደራደሩም፡፡ በሰላማዊ ዜጎች ነብስ አልቆመሩም… ለምን? ከፍ ያለ የሞራል ልእልና ስላላቸው፡፡ የአገር ቫሊዩ ስለገባቸው፡፡
ቄሮ እንግዲህ ‹‹የኦሮሞ ትግል›› በሚል ጓንት የሸፈነውን በንፁሃን ደም የጨቀየ፣ በዘረፋና ዘረኛ ጥፋት የቆሸሸ እጁን ልኮ ነው ይሄንን ሙስሊም ማህበረስብ ሊጨብጥ የሚንጠራራው፡፡ ይህንን የምለው አንዳንድ የቄሮ የቆሸሸ እስስታዊ ባህሪ ያልገባቸው ወገኖች ቄሮ እንዲጮህለት እንደሚፈልገው እስልምና ጋር ለማያያዝ ሲሞክሩ ስላየሁ ነው፡፡ ቄሮ እንደሃረግ የቆመው ላይ ዘሎ ካልተጠመጠመ በራሱ የማይቆም ቡድን ነው …ለዛም ነው ህወሀት ጋርም ሲመቸው ደግሞ ግብፅ ጋር …እየተጥመለመለ ጥፋቱን የቀጠለው! የቄሮ ሐይማኖት …የሰው ልጆችን ሁሉ መጥላት እና የበታችነት ብቻ ነው!! ከዚህ ህመሙ የሚፈውሰው ደግሞ ጠንካራ የፍትህ ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ ብቻ ነው፡፡ እደግመዋለሁ የቄሮ ደም የጠማው አራጅነት ከኦሮሞም፣ ከክርስቲያንም፣ ከሙስሊምም ሆነ ከጥቁር ህዝቦች ትግል ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም!