በግብፅና ሱዳን ጥያቄ የተቋረጠው የሦስትዮሽ ድርድር የፊታችን ሰኞ ቀጠሮ ተይዞለታል ተባለ

በግብፅና ሱዳን ጥያቄ የተቋረጠው የሦስትዮሽ ድርድር የፊታችን ሰኞ ቀጠሮ ተይዞለታል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከሥራ ውጭ የሆኑ፣ በእስር እና በስደት ላይ የነበሩ 218 ዜጎች ባለፉት 2 ሳምንታት ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሱ ተነገረ።

የውጭ ጉዳይ የሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ  ዛሬ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ በተለያዩ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከሥራ ውጭ የሆኑ፣ በእስር እና በስደት ላይ የነበሩ 218 ዜጎች ባለፉት 2 ሳምንታት በዜጋ ተኮር ፖሊስ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ መደረጉን በመግለጫቸው ላይ አንስተዋል።
 በቤይሩት በደረሰው የፍንዳታ አደጋ የአንድ ኢትዮጵያዊ ሕይወት ሲያልፍ በ9 ኢትዮጵያውያን ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው መንግሥት ማረጋገጡንም አስታውቀዋል።
 ጉዳቱ ሠፊ መሆኑን ተከትሎ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ተጨማሪ ዜጎች ስለመኖራቸው  ቆንስላ ጽሕፈት ቤቱ የማጣራት ሥራ በማከናወን ላይ መሆኑንም ቃል አቀባዮ ጠቁመዋል።
በተያያዘ ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ላይ የውሃ ሙሌት ደንቧን ማቅረቧን የተናገሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ሆኖም ድርድሩ ሁለቱ ሀገራት ደንቡን ለመመልከት ቀን ይሰጠን በማለታቸው መቋረጡንም ይፋ አድረገዋል።
 በድርድሩ ላይ ከግድቡ ጋር በማይገናኝ መልኩ በዘላቂ የውሃ አጠቃቅም ዙሪያ ከስምምነት እንድረስ በሚል እየተነሳ ያለውን ጥያቄ ኢትዮጵያ እንዳልተቀበለችውም ከመግለጫው መረዳት ተችሏል።
በድርድሩ ኢትዮጵያ የአባይ ውሃን  ዘላቂ አጠቃቀም በተመለከተ በሌላ ድርድር የሚታይ እና ሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት በተካተቱበት ሁኔታ ብቻ ድርድር ይካሄዳል በሚል አቋሟ መጽናቷን ቃል አቀባዮ አስታውቀዋል። አሁን ላይ የተያዘው ቀጠሮ የቀን ለውጥ ከሌለው  ኢትዮጵያ የሦስትዮሽ ድርድሩ በመጭው ሰኞ  ይቀጥላል ብላ እንደምታምንም ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY