በአፋር ክልል አሁንም 51 ሺኅ ሰዎች በጎርፉ ሳቢያ ስጋት ላይ ናቸው ተባለ

በአፋር ክልል አሁንም 51 ሺኅ ሰዎች በጎርፉ ሳቢያ ስጋት ላይ ናቸው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ ባስከተለው ሰሞነኛ የጎርፍ አደጋ 49 ሺኅ 65 ሰዎች መጠቃታቸውንና የችግሩ መጠን ከፍ  ማለቱን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ገለጸ።

የቢሮው ምክትል ሓላፊ ወይዘሮ ኩልሱማ ቡርሃባ አሊ  በማዕከላዊና ታችኛው አዋሽ በስጋት ቀጠናነት ከተለዩት 17 ወረዳዎች መካከል 10ሩ በጎርፍ አደጋ መጠቃታቸውን ጠቁመው፤ይህን ተከትሎ19 ሺኅ 656 ሰዎች መፈናቀላቸውን በእንስሳት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል።
በጎርፉ ሳቢያ 51 ሺኅ 659 ሰዎች ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ የተናገሩት ሓላፊዋ፤ አሁን ላይ ከጎርፍ አደጋው ጋር በተያያዘ በ5 ወረዳዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ የማድረግና ከመከላከያ ጋር በመተባበር በሄሊኮፕተር የነብስ አድን ሥራው በተጠናከረ ሁኔታ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
እየወጡ ያሉ የአየር ትንበያ መረጃዎች በቀጣይ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል አመላካች መሆናቸውን ተከትሎ ነዋሪዎችን ወደ ከፍተኛ ቦታዎች የማዘዋወር እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ እየተካሄደ መሆኑም ተገልጿል፡፡

LEAVE A REPLY