ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ትናንት ማምሻውን በቦሌ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ከፍተኛ የሆነ የንብረት ውድመት መድረሱ ተሰማ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል አየርአምባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት አመሻሽ ላይ ነው ይህ ከባድ አደጋ የደረሰው።
የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት የከተማው የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር መዋሉን የቦሌ ክፍለ ከተማ የሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ጉልላት ከበደ አረጋግጠዋልተ
የአደጋውን መንስዔ እና በንብረት ላይ የደረሰውን ውድመት በተመለከተ ፖሊስና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በማጣራት ላይ እንደሆነም ተነግሯል።

























