የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለቀጣዮ ምርጫና ህወሓት ያካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ለዲፕሎማቶች ገለጻ አደረገ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለቀጣዮ ምርጫና ህወሓት ያካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ለዲፕሎማቶች ገለጻ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢፌዴሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተራዘመውን 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ እና የትግራይ ክልል ኢ-ህገመንግሥታዊ ምርጫ ማካሄዱን አስመልክቶ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ማብራሪያ ሰጠ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ በሚገኝበት ወቅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመከሰቱ ምርጫው የተራዘመ መህኑን ያስታወሰው ሚኒስቴሩ፤ በአሁኑ ሰዐት ወረርሽኙ መች እንደሚያበቃ ባለመታውቁ እና እንቅስቃሴ በመጀመሩ ምርጫ በያዝነው ዓመት እንዲከናወን ምክር ቤቱ መወሰኑን አስታውሷል።
የትግራይ ክልል መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዳይካሄድ በወሰነበት ሁኔታ ውስጥ ምርጫ ማካሄዱ በፌደራል መንግሥት ተቀባይነት እንደለሌውም  በአዲስ አበባ ለሚገኙ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
የትግራይ ክልል መንግሥት ኢ- ህገመንግሥታዊ ምርጫ በማካሄዱ ፌደራል መንግሥት ከክልል የበላይ አስተዳደር ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጦ ከዞን፣ ከወረዳ እና ከቀበሌ ጋር ግንኙነት እንዳለውም ነው የተነገረው።
የትግራይ ክልል ሕዝብ እንደ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የምግብ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ እንዲሁም የትምህርት እና መሰል መሠረታዊ አገልግሎቶች በተገቢው ሁኔታ እንዲያገኙ የፌደራል መንግሥት እንደሚሠራም በገለጻው ላይ ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY