ዘመናዊው የኦንጦጦ ፓርክ ዛሬ በይፋ ተመረቀ፣ ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኗል

ዘመናዊው የኦንጦጦ ፓርክ ዛሬ በይፋ ተመረቀ፣ ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኗል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ ለክፉ እጃቸውን የሚያነሱ ብቻ ሳይሆን ሀገራቸውን ለመቀየር የሚተጉ ዜጎች ያሉባት ሀገር መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

” የዛሬ አመት መስከረም 29 ቀን 2012 ዓም የአንድነት ፓርክን ስናስመርቅ በነጋታው የእንጦጦ ፓርክን ሥራ እንደምንጀምር አስታውቀን ነበር” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በነጋታው መስከረም 30 እኔና ጥቂት ጓደኞቼ ወደዚህ ስፍራ ስንመጣ ዛሬ የምናየውን ውብ ቦታ ማየት የማይቻልም ነበር ” ሲሉ ዛሬ በይፋ ስለተመረቀው እንጦጦ ፓርክ አጀማመር ትውስታቸውን አጋርተዋል።
ኢትዮጵያ ብርቱና የሚያስቡትን መተግበር የሚችሉ ወጣት ባለሙያዎች ያላት በመሆኑ ይህን ውብ ስፍራ በአጭር ግዜ እውን ለማድረግ መቻሉን ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ እነዚህ ባለሙያ ወጣቶች ቀንና ማታ ሰርተው በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ፣ በየትኛውም መመዘኛ የማያሳፍር ሥራ ሠርተዋልና እነዚህ እጆች ሊመሰገኑ ይገባልም በማለት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
“በምትሄዱበት የሀገሪቱ አካባቢዎች በሙሉ እንደዚህ አይነት ውብ ሥፍራዎችን ለመሥራት ምች የሆኑ ቦታዎች አሉ ” በማለት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከተባበርን በየአመቱ ሌሎች መሰል ውብ ስፍራዎችን መገንባት እንችላለንም ብለዋል፡፡
እንጦጦ ፓርክ የአሁኑን ገጽታ እንዲላበስና ውብ ሆኖ እንዲታይ በሀሳብ፣ በገንዘብ፣ በጉልበት እና በብዙ መንገዶች ድጋፍ ላደረጉ አካላትና ግለሰቦች ምስጋና ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶችም በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚጠናቀቁ ቃል ገብተዋል።

LEAVE A REPLY