ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሁመራና አካባቢው ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር መዋሉን የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል መሐመድ ተሰማ ገለፁ።
ሠራዊቱ በአሁኑ ሰዐት ከሁመራ እስከ ሽራሮ ያለውን ቦታ በማጥቃት የተለያዩ ሥፍራዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝና ሠራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የእርዳታ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ተነጋግረው ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉም አስረድተዋል።
የህወሓት ጁንታ በአልመዳ ርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሠራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ፣ ኤርትራ እንደወረረች በመግለጽ ሕዝብን እያደናገረ እንደሆነም ሓላፊው ተናግረዋል።
በተቀነባበረው ድራማ ሕዝቡ ሳይታለል ለመከላከያ ሠራዊቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ቀርቧል።

























