ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ምርጥ ዒላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ ማድረጉን የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገለፁ።
አየር ሀይሉ ለጁንታው እስትንፋስ የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎች ፣ የመሣሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ምርጥ ዒላማዎችን ያለምንም ከልካይ ጀቶች ማውደሙን አዛዡ ከሰጡት መግለጫ መረዳት ተችሏል።
ፓይለቶቹ የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው በሚሄዱበት ወቅት ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ፣ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂን እየተከተሉ እንደሚገኙም ታውቋል።
ተመትቶ ወድቋል ስለተባለው ጄት አስተያየት የሰጡት ሜ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ፤ ጁንታው እድሜውን ሁሉ ሲዋሽ ስለኖረና እየዋሸ ስለሚቀበር ባህሪው ነው ካሉ በኋላ፤ አሁንም ቡድኑ ለህግ እስኪቀርብ ድረስ አየሩ ኃይሉ ጥቃቱን እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

























