በአብዬ ግዛት የነበረው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ግዳጁን ማጠናቀቁ ተሰማ

በአብዬ ግዛት የነበረው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ግዳጁን ማጠናቀቁ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በአብዬ ግዛት የተሰማራው የ22ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ግዳጁን አጠናቆ ለተተኪው ለ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ማስረከቡ ተነገረ።

የ22ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አመራርና አባላት በነበራቸው የግዳጅ ቆይታ ስኬታማ ሥራዎች አከናውነዋል ያሉት የዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የኃይል አዛዥ ሜጄር ጀነራል ከፍያለው አምዴ፤ በርከክቡ ወቅት የሰላም አስከባሪ ሻለቃው የአካባቢው ማኅበረሰብ ጎሳዎች እርስ በርስ ተከባብረው እንዲኖሩና ችግሮቻቸውን በጋራ ተጠቃሚነት መርህ እንዲፈቱ ባደረገው የማወያየትና የማደራደር ሥራ በህብረተሰቡ ዘንድ አክብሮት እንዳስቻለው ገልጸዋል።
የ22ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ሰለሞን ተስፋ በበኩላቸው፤ የተሰጣቸውን ቀጣና የዲንካና የሚስሪያ ጎሳዎች የጋራ መጠቀሚያ የሣር ግጦሽ እና የውሃ ኩሬ ያለበት በመሆኑ፣ ሁለቱም ጎሣዎች ሳይጋጩ በጋራ እንዲጠቀሙ ከማድረግ ባሻገር፣ ችግሮች ሲከሰቱም በመፍታት ሀገሪቱ የሰጠችውን ግዳጅ አጠናቀናል ሲሉ ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY