ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚወጡት የህግ ማዕቀፎች ክፍተት አለባቸው

ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚወጡት የህግ ማዕቀፎች ክፍተት አለባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች ቢወጡም የአፈፃፀም ክፍተት እንዳለባቸው ተነገረ።

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ጋር “ሰላም ለሴቶች፣ ከጓዳ እስከ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት ዛሬ አካሂዷል።
በዚህ ውይይት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ቢኖርም፣ አሁንም የአፈፃፀም ክፍተት እንዳለበት ባለሙያዎቹ አንስተው፤ የህግና የፖሊሲ አፈፃፀም ጉድለትን ለማሳየት ወጣቶችና ሴቶች በሁሉም መልኩ ተሳታፊ መሆን ይገባቸዋል ተብሏል።

LEAVE A REPLY