ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በከተማዋ በሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚያስተምሩ መምህራን ይከፍል የነበረውን የቤት ኪራይ አበል ማሻሻሉ ተሰማ።
መንግሥት በከተማው ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን የመኖርያ ቤት መስጠቱ የሚታወቅ ቢሆንም፤ በወቅቱ ቤት ማግኘት ላልቻሉ መምህራን በፍጥነት ቤት ማዘጋጀት አለመቻሉን ተከትሎ 800 ብር የቤት ኪራይ አበል ሲከፍል ቆይቷል።
ግን ይህ ክፍያ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር የሚመጣጠን አለመሆኑ ግምት ውስጥ ገብቶ የከተማ አስተዳደሪ ዛሬ ባካሄደው የካቢኔ ስብሰባ ፤ ከአሁን በፊት ይከፈል የነበረው የቤት አበል (850 ብር) ወደ 3 ሺሕ ብር እንዲሻሻል መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል።