የሲሚንቶ ዋጋ መናር የኮንስትራክሽኑን ዘርፍ በእጅጉ ጎድቶታል ተባለ

የሲሚንቶ ዋጋ መናር የኮንስትራክሽኑን ዘርፍ በእጅጉ ጎድቶታል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መናር በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ሁለንተናዊ ቀውስ ከመፍጠሩ ባሻገር ፕሮጀክቶች እንዲጓተቱ ምክንያት ሆኗል ተባለ።

በአሁኑ ወቅት በተለይ በሲሚንቶና በአርማታ ብረት ላይ ያለው የዋጋ ንረት የፕሮጀክቶችን ግንባታ እንዲቆም በማድረግ ሀገሪቱን ወደ ችግር ውስጥ እያስገባት መሆኑን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አስታውቋል።
በተለያዩ መንግሥታዊ ግዢ ፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች በኩል የሚታዩ ኢ- ፍትሀዊ የግንባታ አገልግሎት ግዢ አፈፃፀም ሂደቶች ዘርፉን እየተፈታኑት ነው ያለው ማኅበሩ፤ በተጨማሪም በባንኮች በኩል እየተተገበሩ ባሉ የአሠራር ሥርዓቶች ምክንያት በግንባታ ተቋማት ላይ እየተፈጠሩ ያሉ የአሠራር ማነቆዎች ተጨማሪ የዘርፉ እንቅፋቶች ናቸው ብሏል።

LEAVE A REPLY