በሰንደቅ ዓላማ ምክንያት የታሰሩት የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ ረፋድ ላይ ተፈቱ

በሰንደቅ ዓላማ ምክንያት የታሰሩት የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ ረፋድ ላይ ተፈቱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ትናንት በድምቀት የተከበረውን የአደዋ ድል በዓል ተከትሎ በያዙት ኢትዮጵያዊ ሰንደቅ ዓላማ ምክንያት ለእስር ተዳርገው የነበሩ ወጣቶች መፈታታቸው ታወቀ።

   ከታሪካዊው ድል ባሻገር የሀገር ባለውለተኞቹ አፄ ምንሊክ እና ጣይቱ የሚወደሱበት ታላቁ ክብረ በዓል ላይ በርካታ የአዲስ አበባ ወጣቶች አደዋ ላይ የተውለበለበው ንጹሕ ሰንደቅ ዓላማ ያውለበለቡ ወጣቶች በክብረ በዓሉ አካባቢ ችግር ባይገጥማቸውም ወደየአካባቢያቸው ሲመለሱ በርካቶች በፖሊስ ታፍሰዋል።
  አደዋን በአረንጎዴ፣ ቢጫ፣ ቀዮ ሰንደቅ ዓላማ ድምቀት የሰጡት እነዚህ የአዲስ አበባ ወጣቶች ከክብረ በዓሉ መጠናቀቅ በኋላ ወደ ሰፈራቸው ሲመለሱ፤ “ሕገ መንግሥቱ ከፈቀደው ውጪ የሆነ ባንዲራ ይዛችኋል” በሚል በጅምላ እየታፈሱ በፖሊስ ተቋማት ውስጥ እንዲከማቹ ተደርጓል።
  እርምጃውን ተከትሎ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሕዝብ ተቃውሞውን በማስተጋባቱ በርካታ ወጣቶች ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር መፈታታቸውን አረጋግጠናል።

LEAVE A REPLY