ባልደራስ ሆቴሎች መንግስትን በመፍራታቸው አገልግሎት ለማግኘት ተቸግሪያለሁ አለ

ባልደራስ ሆቴሎች መንግስትን በመፍራታቸው አገልግሎት ለማግኘት ተቸግሪያለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የፓርቲው ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ የታሰረበት ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴሎች በመፍራታቸው ያቀድኳቸውን የውይይት ሀሳቦች ለሕዝብ ለማድረስ ችግር ገጥሞኛል አለ።

ፓርቲው ቀደም ባሉት ጊዜያት ተደጋጋሚ የፕሮግራም እግዶች በሆቴሎች እና በተለያዮ አዳራሾች እንደገጠሙት ይታወሳል።
“ሆቴሎች አገልግሎት ለመስጠት በመፍራታቸው በተለያዩ ጊዜያት ሊደረጉ የነበሩ የፓርቲው ውይይቶችን እና መግለጫዎችን ለማካሄድ ተቸግሬአለሁ” ያለው ፓርቲው፤ የአዲስ አበባን የራስ ገዝ ጥያቄ አስመልክቶ ባለፈው ሀሙስ በሀርመኒ ሆቴል ባለሙያዎች የሚሳተፉበት የውይይት ለማካሄድ አስፈላጊውን ክፍያ ቢፈጽምም በዋዜማው ምሽት ላይ ሆቴሉ በስልክ በደፈናው ፕሮግራሙን ለመሰረዝ እንደተገደደ ያሳወቀው መሆኑን ገልጿል።
ሆቴሎቹ በይፋ ምክንያታቸውን ባይገልጹም ከውስጥ ምንጮች በተገኘ መረጃ መሠረት በመንግሥት የሚደረግባቸውን ጫና በመፍራት አገልግሎት የመስጠት ሀሳባቸውን እየቀየሩ እንደሚገኙ የገለጸው ፓርቲው በቀጣዮ ቅዳሜ ባልደራስ ይህንን ፕሮግራም ለማዘጋጀት በመዲናዋ የሚገኙ የተለያዮ ታዋቂ ሆቴሎችን ቢያነጋግርም፤ አሁንም ተመሳሳይ ችግር እየጠጠመው እንደሚገኝ አስታውቋል።
ባልደረስ ከተመሰረተበት ጊዜ አነሰቶ የሚጠራቸው ስብሰባዎች እና ሰለማዊ ሰለፈች ላይ በታጣቂዎች እና በፖሊስ አካላት ወከባና እንግልት ሲደርስበት መቆየቱ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY