ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአገራችን ከሚገኙ 182 የከረሜላ ፋብሪካዎች ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ደረጃቸውን የጠበቁ እንዳልሆኑ ተሰማ።
የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የምግብ አምራች ተቋማት ኢንስፔክተር ህሊና ተስፋዬ፤ በተለያየ ጊዜ ፋብሪካዎች ላይ ድንገት ፍተሻዎችን መደረጉን ተከትሎ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ፋብሪካዎች ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ጥሬ ዕቃን ከመጋዘን ውጪ ማከማቸት፣ የመሥሪያ ቦታ ንጽሕና መጓደል እና የሠራተኞች በጥንቃቄ አለመሥራት የችግሩ ዋነኛ ምንጮች እንደሆኑ የሚያስረዳው ተቋሙ፤ ይህ ችግር አሁን ባለው ደረጃ ለሰው ሕይወት አስጊ ባይሆንም ወደ ፊት የከፋ ነገር ሊከሰት እንደሚችል ግምቱን ከወዲሁ አስቀምጧል።