ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት በ “ጽኑ የሚታመሙ” ሰዎች ቁጥር እጅግ በመጨመሩ በአገሪቱ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ የኦክስጅን እጥረት ማጋጠሙ ተሰማ።
አሁን ላይ 600 በላይ ከፍተኛ ክትትል እና የፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች እንዳሉ ሲታወቅ፣ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር በየቀኑ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ያዕቆብ ሰማን በበኩላቸው፣ በፍጥነት የወረሽኙን የመከላከያ መንገዶች ትግበራ ወደ አስገዳጅነት እንዲገባ ካልተደረገ እና ሁሉም በሚገባ ካልተጠነቀቀ የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል አስገንዝበዋል።