በአዲስ አበባ የ”ሹገር ማሚዎች” መበራከት እያነጋገረ መሆኑ ተሰማ

በአዲስ አበባ የ”ሹገር ማሚዎች” መበራከት እያነጋገረ መሆኑ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ በተለምዶ “ሹገር ማሚ” ተብለው የሚጠሩ በዕድሜ የገፉና ለአንቱታ የቀረቡ ሴቶች፣ የልጃቸው እኩያ ከሚሆኑ ወጣቶች ጋር አንሶላ ለመጋፈፍ፣ በቀን እስከ 9 ሺ ብር ድረስ እንደሚከፍሉ ተሰምቷል፡፡

ሸገር 102.1 ሬድዮ እንደዘገበው፣ እነዚህን በዕድሜ የገፉ ሴቶች ለማግኘት አገናኝ ኤጀንሲው ከወንዶቹ  550 ብር ኮሚሽን የሚቀበል ሲሆን፣ ኤጀንሲው ለዚህ ተግባር የተዘጋጀ  አስር የባንክ አካውንት እንዳለው ታውቋል።

ወንዶቹ  ከሹገር ማሚዎቹ ጋር ያላቸው ቆይታ ለሶስት ቀን ከሆነ 14,000 ብር፣ ለሳምንት ከሆነ ደግሞ 18,000 ብር  እንደሚከፈላቸው የዘገበው ሬድዮው፣ የዚህ አይነት ድርጊት ከሀገሪቷ ባህል ጋር ፈፅሞ የተቃረነ መሆኑንም አመልክቷል።

LEAVE A REPLY