ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሸባሪው የህወሓት ቡድን በትምህርት ተቋማት ላይ በፈፀመው ውድመት የክፋት ጥጉን አሳይቷል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች ጋር አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ወሎ ዞን ካወደማቸው መካከል የኮኪት ሁለተኛ ደረጃንና የደብረዘቢጥ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ተመልክተዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ በወቅቱ እንዳሉት፤አሸባሪው ቡድን ያደረሰው ጥፋት የውጭ ወራሪ ቢመጣ ከዚህ የባሰ ጉዳት ሊያደርስ ከሚችለው በላይ ነው።
በዚህም አሸባሪው ቡድን ለዘረፋ ብቻ እንዳልመጣ ድርጊቱ እንደሚያሳይ አስረድተዋል።
”ትምህርት ቤቶችን ወደ ሜዳነት ቀይሯቸዋል” ያሉት ሃላፊው፣የትምህርት ተቋማትን ከማውደሙም በላይ ከኢትዮጵያዊነት ባህል ያፈነገጠ አስነዋሪ ተግባር መፈፀሙን አስረድተዋል።

























