ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በቅርቡ ክሳቸው ተቋርጦ ከዕሥር የተፈቱ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች የመንግሥት ዳግም ዕሥር ማስፈራሪያን እንደማይቀበሉት እና ሠላማዊ ትግል እንደሚቀጥሉ ገለጹ።
መንግሥት ታኅሣሥ 29/2014 ክሳቸውን ተቋርጦ ከዕሥር በፈታቸው ዕሥረኞች ጉዳይ ላይ ጥር 1/2014 በተካሄደው የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት የምረቃ መድረክ ወቅት ባደረጉት ንግግር ማብራሪያ የሠጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ክሳቸው የተቋረጠላቸው ሰዎች የተሠጣቸውን ዕድል በአግባቡ ካልተጠቀሙ የክስ መዝገባቸውን መምዘዝ እንደሚቻል መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ከዕሥር የተፈቱት የባልደራስ አመራሮች በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስፈራሪያ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

























