በአማራ ክልል 116ሺህ መምህራንን ጨምሮ ከ1.9 ሚልዮን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው...

በአማራ ክልል 116ሺህ መምህራንን ጨምሮ ከ1.9 ሚልዮን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአማራ ክልል ጦርነቱ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት ከ1.9 ሚልዮን በላይ ህጻናት እና 116 ሺህ መምህራን ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደሆኑ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የአማራ ክልል የዞን እና የወረዳ አመራሮች በትምህርት አጀማመር ዙርያ በደሴ ከተማ ምክክር ባካሄዱበት ወቅት እንደተነገረው በትምህርት ተቋማት ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት ቁጥራቸው ከ1.9 ሚልዮን የሚበልጥ ህጻናት ከትምህርት ውጭ ሆነዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ማህተም ሽፈራው የእድገታችን ፍጥነት የሚለካው ትምህርት ላይ በምንሰራው ስራ በመሆኑ የፈረሱ ተቋማትን በአጭር ጊዜ ወደ አገልግሎት መመለስ አለብን ብለዋል።

አሁን ከሞላ ጎደል በበርካታ ተቋማት ትምህርት የተጀመረ ሲሆን በስልጠና በቁሳቁስና በገንዘብ ድጋፍም መጠናከሩን የቢሮው ኃላፊው ገልፀዋልገልፀዋል።

LEAVE A REPLY