የአዲስ አበባ ፖሊስ ለጥምቀት በዓል አርማ የሌላቸው ባንዲራ እንዳይያዝ ከለከለ 

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለጥምቀት በዓል አርማ የሌላቸው ባንዲራ እንዳይያዝ ከለከለ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የጥምቀት በዓልን ለማክበር የሚወጣው ምዕመን ግጭት ቀስቃሽ ጽሑፎችን እና አርማ የሌላቸውን ባንዲራ ይዞ መውጣት እንደማይችል አስታወቀ::

ፖሊስ ኮሚሽኑ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለአሀዱ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ምዕመኑ ከበዓሉ አላማ ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን ከማድረግ ተቆጥበው በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል::

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ስጋት በሰላም እንዲጠናቀቅ ከበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ጋር በመሆን የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል::

በዓሉ የአደባባይ በመሆኑ በሁሉም አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር በግልጽና በስውር የተጠናከረ ጥበቃ መኖሩን ጠቅሰዋል።

በዓሉ በሚከበርባቸው ሁለት ቀናት ወደ ማክበሪያ ቦታው መግባት የሌለባቸው ግጭት የሚቀሰቅሱ ጽሑፎች ፣ አርማ የሌለው ባንዲራ እንዲሁም ስለታማ ነገሮች ይዞ መግባት እንደማይቻልም አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል::

LEAVE A REPLY