ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና አምባሳደር ድሪባ ኩማ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው ነው ፍርድ ቤቱ ያዘዘው።
የመጥሪያ ትዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
በነ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው የመርከብ ግዢ የሙስና ክስ ላይ በመከላከያ ምስክርነት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲመሰክሩ ነው መጥሪያ እንዲደርሳቸው የታዘዘው።
በጥር 23 ቀን በነበረው የችሎቱ ቀጠሮ ተከሳሾች እነ ዶ/ር ወርቅነህ መከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡላቸው በጠየቁት ጥያቄ መሰረት ፍ/ ቤቱ መርምሮ ለተከሳሾች በመከላከያ ምስክርነት የሚቀርቡ አካላት መጥሪያ እንዲደርሳቸው ትዛዝ ሰቶበታል።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ሜ/ጀነራል አብዱል ሰላምን እና ኮነሬል ሸጋውን በፌደራል ፖሊስ በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው ያዘዘ ሲሆን ኮ/ል አስመረት ኪዳኔ እና ሻለቃ ሰመረ ሀይሌን ደግሞ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው አዟል። ውጤቱን ለመጠባበቅ ለመጋቢት 8 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል።፧

























