የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ለጎረቤት ሀገራት የሚሸጡ ነጋዴዎች በመኖራቸው ነው ተባለ

የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ለጎረቤት ሀገራት የሚሸጡ ነጋዴዎች በመኖራቸው ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየሰጡት ባለው ምላሽ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከቀጠናው ሀገራት አንፃር የነዳጅ ዋጋ አነስተኛ የሆነባት በመሆኑ ባለሀብቶች እና የቦቴ መኪና ባለንብረቶች ነዳጅ ወደ ጎረቤት ሀገራት እየወሰዱ መሸጣቸው በሀገሪቱ የነዳጅ ዋጋና እጥረት ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል ብለዋል።

መንግስት የነዳጅ ፍላጎትን በመደጎሙ የተፈጠረውን የዋጋ መቀነስ ዘራፊዎች ጥቅሙን አሳልፈው ለሌሎች ሀገራት መሸጣቸው ችግር ፈጥሯል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ነዳጅ ጭነው ከድንበር ለመዉጣት የሚሞክሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ካዋሉ ተሽከርካሪዎቹንም ነዳጁንም እንዲወርሱ መመሪያ መሰጠቱን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአዲስ አበባ የነዳጅ ማደያዎች የነበረውን መጨናነቅ ተከትሎ የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም. እንደገለፀው የአቅርቦት እጥረት አለመኖሩን መግለፁ የሚታወስ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥር ወር እንደተገለፀው የነዳጅ ድጎማ ከግሉ ዘርፍ ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲነሳ እና ለመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ደግሞ ድጎማው ቀስ በቀስ እየተነሳ በአምስት ዓመታት ውስጥ እንዲያልቅ በመመሪያ መወሰኑ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY