በደካሞቹ ላይ – አትሰልጥን ሲል ቃሉ ፣
ለብርቱዎች ነበር – ምክር ማቀበሉ ….፤
ዳሩ ምን ያደርጋል ? – ሰሚ ጆሮ ጠፋ፣
ብርቱው ግፍ አበዛ – ደካማው ተገፋ ..፤
ይፈጸም ዘንድ ቃሉ! – ዛሬ ግድ ሆነና ፣
ብርቱን ብርቱ ገፋው! – ወር ተራ ገባና ፤
ይልቅ አንተ ስማኝ ……
ወረተኛው ግዜ – ነገ ፍቅሩ አልቆ፤
የቸረህን ብርታት – ሳይወስድብህ ነጥቆ፤
የሰላምን ማሳ – ጎልጉል እረስበት፤
የፍቅርን ችግኝ – አፍላ ትከልበት ….፤
በግዜ ንቀለው – ክፉ አረም ነው ጸጸት፤