የኢትዮ- ቴሌኮም የደንበኞቹ ቁጥር ከ60 ሚሊየን ማለፋን አስታወቀ

የኢትዮ- ቴሌኮም የደንበኞቹ ቁጥር ከ60 ሚሊየን ማለፋን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮ- ቴሌኮም የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ዛሬ የካቲት 21 2014 በሂልተን ሆቴል በገንዘብ ሚኒስቴርና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በተገመገመበት ወቅት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የድርጅታቸው አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 60 ነጥብ 8 ሚሊየን መድረሱን አስታውቀዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ አንዳሉት በዘንድሮ ግማሽ ዓመት ድርጅቱ 28 ቢሊየን ብር ግቢ ማገኘቱን ተናገረው 74 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ከስምንት ወር በፊት ሥራ ላይ ባዋለው የቴሌ ብር አገልግሎት 13 ነጥብ 1 ሚሊየን ደንበኞችን በማፍራት 16 ነጥብ 6 ሚሊየን ክፍያዎች በመተግበሪያው አማካኝነት መደረጉንና በገንዘብ ረገድም የ5 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ልውውጦች መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ወጪውን ለመቀነስ እንዲያስችለው ዱቱሴቭ አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ማስቀረት ችያለሁ ያለው ድርጅቱ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለዕዳ ክፍያ ማዋሉን እንዲሁም 12 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር የታክስ ክፍያ መፈፀሙንም ገልጿል፡፡

ከግማሽ ዓመቱ ዕቅዴ 86 በመቶውን ነው ያሳካሁት ያለው ድርጅቱ የፀጥታ ችግር የመስረተ ልማትና ንብረት ጉዳት በክልሎች አግባብ ያልሆነ ካሳ ጥየቃና የባንክ ሂሳብ መዘጋት ለሥራዬ ዋና ዕንቅፋት ነበሩ ሲልም አስታውቋል፡፡

የግምገማ መድረኩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር አህመድ ሽዴ እንዳሉት ኢትዮ ቴሌኮም ባለፋት 6 ወራት ውስጥ አገልግሎቱን በማስፋፋት የአግልግሎቱን ጥራት በማሻሻልየገጠሙትን ፈተናዎች ለማለፍና በተለይ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት በኩል ጠንክራ ሥራ ሰርቷል ብለዋል።

LEAVE A REPLY