ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ከዚህ ዓለም...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ በጠና ታመው ሲታከሙ ቆይተው ትናንት ምሽት በ84 አመታቸው ማረፋቸው ተሰምቷል፡፡

በቀድሞ አጠራሩ በበጌምድር ጠቅላይ ግዛት የተወለዱት ብፁዕ ወቅደስ አቡነ መርቆርዮስ በየደረጃው ያሉትን የተወሀዶ ሃይማኖት ትምህርት ሲከታተሉ የወጣትነታቸውን ጊዜ አሳልፈዋል፡፡

አባ ዘሊባኖስ ፈንቴ በሚለው ስማቸው እስከሚታወቁበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከድቁና እስከ ደብር አለቃነት አገልግለዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ለጳጳስነት ተመርጠው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ሲመቱን የተቀበሉት ገና የ38 ዓመት ጎልማሳ በነበሩበት ጊዜ ነው፡፡

በሊቀ ጳጳስነት በተመደቡበት ጎንደር ክፍለ ሀገር የፓትርያርክነት ማዕረግ አስኪቀበሉ ድረስ አገልግለዋል፡፡
አራተኛው ፓትርያርክ ሆነው ከተሰየሙ ሶስት አመት በኋላ በነበረው የሥርዓት መንግስት ለውጥ በህወሀት ከፍተኛ ባለሰልጣናት ተገደው መነበረ ስልጠናቸውን እንዲለቁ ተደርገዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በመጀመሪያ በኬንያ በመቀጠልም ለረጀም አመታት በስደት በአሜሪካ በቆይተዋል።

በስደት በነበሩበት ፓትርያርክ በሕይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ እነደማይሾም የሚደነግገውን የቀደምት አባቶች ቀኖና ህግ ተግበራዊ በማድረግ በውጭ ሀገር በቅዱስነታቸው ፈቃድ ቀዱስ ሲኖዶስ ሰቋቁመው በስደት የመገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮችን ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከ26 ዓመታት ስደት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፣ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር የፓትርያርክነት አገልግሎታቸውን በጋራ  እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡

አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበሩ መገለፁ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY