ከሳኡዲ አረቢያ፣ ጂዳ 269 ህጻናትን ጨምሮ 1 ሺህ 270 ዜጎች ወደ አገራቸው...

ከሳኡዲ አረቢያ፣ ጂዳ 269 ህጻናትን ጨምሮ 1 ሺህ 270 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በዛሬው ዕለት ከሳኡዲ አረቢያ፣ ጂዳ በተደረጉ ሦስት በረራዎች 269 ህጻናትን ጨምሮ 1 ሺህ270 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

በሳውዲ አረቢያ፣ በሪያድ እና የጅዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ተግባር መቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ተመላሾች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች እና ማዕከላት ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ አገር ቤት ማምጣቱ፤ በሳምንት ለሦስት ቀናት በቀን ሦስት ግዜ በሚደረግ በረራ የመመለሱ ሥራ እንደሚቀጥልም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

LEAVE A REPLY