ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፀጥታ ኃይሎች መወሰዱ ታወቀ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፀጥታ ኃይሎች መወሰዱ ታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሳምንታዊው የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን ወንድሙ ተናገሩ።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ የጋዜጠኛው የሥራ ባልደረቦች በሁለት መኪና የመጡ ሲቪል የለበሱና የፀጥታ ኃይሎች ነን ያሉ ሰዎች ይዘውት ሄደዋል ብሏል። የወሰዱት ሰዎች  ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአመት በፊት ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከመጽሔት ሥራው ጋር በተገናኘ ለአንድ ቀን ታስሮ መለቀቁ ይሚታወስ ሲሆን ጋዜጠኛው በኢሕአዴግ ዘመን በሚሰራቸው የሕትመት የጋዜጠኝነት ሥራዎቹ ምክንያት ለዓመትት ታስሮ እንደነበርም አይዘነጋም።

በተያያዘ ዜና ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ከመኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ኃይሎች ተወሰደ ኢትዮ ፎረም‘ የተሰኘው የዩቲዩብ ገፅ አዘጋጅ የሆነው ያየሰው ሽመልስ በፀጥታ ኃይሎች ከመኖሪያ ቤቱ ተወሰደ።

ዛሬ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ ከተማ የካ አባዶ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች መወሰዱን የጋዜጠኛው ጠበቃ አረጋግጧል። ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በፀጥታ ኃይሎቹ ከተያዘ በኋላ በቅድሚያ ወደ የካ አባዶ ፖሊስ ጣቢያ በመቀጠልም ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዷል።

LEAVE A REPLY