በአማራ ክልል 16ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል

በአማራ ክልል 16ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አማራ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለው ግጭትና ጦርነት እስካሁን እስከ 16 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዳወደመ የክልሉ መንግሥት ገለጸ።

በአማራ ክልል ካለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ጀምሮ በክልሉ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሕይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ መዝለቁን  በርካታ ሰብአዊ ቀውስ መፍጠሩንም የአማራ ክልልላዊ መንግስት ክፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል። 

ጦርነት በጦርነት አይጠናቀቅም ያሉት የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ችግሮችን በውይይትና በሰላም ለመፍታት የመንግሥት በሮች ክፍት መሆናቸውን ገልጸዋል ።

የቢሮው ኃላፊ   በክልሉ እየተካሄደ ባለው ጦርነት «አንዳንድ የመንግሥት ኃይሎች በንፁሐን ላይ ከሕግ ውጭ ጥቃት ይፈፅማሉ» ተብለው የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ «የፀጥታ ኃይሉ በእስካሁኑ ሂደት በስሌትና በጥንቃቄ እየሠራ ነው»  ሆኖም እንደተባለው ያለ ድርጊት በተጨባጭ ከተፈፀመ  ግን መንግሥት ድርጊቱን ገምግሞ ማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል» ብለዋል።

በክልሉ የመንግስት ወታደሮች በርካታ ከጦርነቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ንፁሀን እየተገደሉ መሆኑን ዘጋቢዎች ያስረዳሉ። በቅርቡ በመራዊ ከተማ የመንግሥት ወታደሮች ባደረሱት ጥቃት ወደ 50 የሚጠጉ ንፁሀን ዜጎች እንደተገደሉ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። en

LEAVE A REPLY