በሞቃድሾ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አቅራቢያ የሽብር ጥቃት ተሰነዘረ

በሞቃድሾ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አቅራቢያ የሽብር ጥቃት ተሰነዘረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሶማሊያ ዋና ከተማ  ሞቃዲሾ ውስጥ አሸባሪዎች ሃሙስ መጋቢት ፮ቀን/፪ሺህ፩፮ በፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት አቅራቢያ የሚገኘውን ሲልል ሆቴል ላይ  ጥቃት መሰንዘራቸውንነዋሪዎች ተናገሩ። የሮይተርስ  ከአይን ምስክሮች እንደአረጋገጠው።

የሃሙስ ማምሻውን ፍንዳታ ተከትሎ የተኩስ እሩምታ ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናት እና የህግ አውጭዎች መሰብሰቢያ በሆነው ሲልል ሆቴል ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘራቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

በፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት አቅራቢያ የሚኖሩ ነዋሪ የሆኑት ፋራህ አሊ “መጀመሪያ ከፍተኛ ፍንዳታ ሰማን ከዛም የተኩስ ድምጽ ተከሰተ። ተዋጊዎቹ በሆቴሉ ውስጥ እንዳሉ ተረድተናል ምክንያቱም የተኩስ ልውውጥ ስለሰማን ነው” ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

 በዚሁ የሽብር ጥቃት በትንሹ 10 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ነዋሪዎቹ ለየሮይተርስ ተናግረዋል። ከመጀመሪያው ፍንዳታ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሁለተኛ ፍንዳታ እንደሰማ  በስፍራው የነበረ የአይን ምስክር ተናግሯል። ስለተከስተው አደጋ እና ስለጉዳቱ መረጃ ለማግኘት ፖሊስ እና ሌሎች የመንግስት ቃል አቀባዮች አስተያየት  ለማግኘት አልተቻለም። ብሏል የሮይተር ዘጋቢ። ዘግይቶ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው አልሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ወስዷል። en

LEAVE A REPLY