ዐቃቤህግ የእነመስከረም አበራ ክሳቸውን በቪዲዬ እንዲከታተሉ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገበት

ዐቃቤህግ የእነመስከረም አበራ ክሳቸውን በቪዲዬ እንዲከታተሉ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገበት

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ፣ መስከረም አበራን ጨምሮ 23   በማረሚያ የሚገኙ ተከሳሾች የፍርድ ቤቱ አካባቢን በጩኸት በማወክ ረብሸዋል ስለዚህ በአካል ሳይቀርቡ ክርክራቸውን በቪዲዮ ኮንፍረንስ ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ዐቃቤ ህግ እንዲታዘዝለት ባቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደረገበት።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የህገ መንግስትና በህገ መንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት በሽብር ወንጀል በተከሰሱት እነ  ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ  መዝገብን ለመመልከት መጋቢት 6 ቀን/2016 በዋለው ችሎት ነው የዐቃቤ ህግን አቤቱታ ውድቅ ያደረገው።

የተከሳሾች ጠበቆች በዐቃቤ ህግ የቀረበው ችሎት ሳይቀርቡ ባሉበት በቪዲዮ ኮንፍረንስ ክርክራቸውን እንዲያደርጉ ያቀረበው አቤቱታ የህግ አግባብነት እንደሌለው ጠቅሰው መልስ ሰጥተዋል።

ፍርድ ቤቱም መርምሮ ተከሳሾቹ ስነ-ስርዓታዊ ህጉን ተከትለው ክርክር ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝቧል። በህገመንግስቱ በተሰጠ መብት መሰረት ተከሳሾች በአካል ቀርበው የመከራከር መብታቸውን ፍርድ ቤቱ ከግምት ውስጥ ማስገባቱን ጠቅሶ፤ በድጋሚ የፍርድ ቤቱን ስርዓት የሚጥስ ተግባር እንዳይፈጽሙ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸዋል።

በድጋሚ ፈጽመው ቢገኙ ግን ያለምንም ቅድመ ሀኔታ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ችሎቱ ገልጾ ብይን ሰጥቷል።

ችሎቱ በዛሬው ቀጠሮ ከአማራ ክልል ጋር ተያይዞ በሽብር ወንጀል በተከሰሱት እነ ወንደሰን አሰፋ (ዶ/ር) መዝገብ ተካተው ባልቀረቡ ምሬ ወዳጆን ጨምሮ 27 ተከሳሾች የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግና እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በዚህ መልኩ ፍርድ ቤቱ የጋዜጣ ጥሪ ለመጠባበቅና ከዚህ በፊት ዐቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ ላይ ጉዳት ደረሰባቸው የተባሉ ግለሰቦች ማንነትን በማካተት አሻሽሎ እንዲያቀርብ በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ውጤቱን ለመጠባበቅ ለሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። en

LEAVE A REPLY