ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአፍሪካ ኀብረት አስፈጻሚዎች ምክር ቤት 22ኛ ልዩ ስብሰባ በቀጣዩ አመት የሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ለኮሚሽኑ ሊቀ መንበርነት ምርጫን በተመለከተ የመወዳደርያ መስፈርቶችን አፅድቋል። ይህንንም ተከትሎ ኬንያ አህጉራዊ ዘመቻ ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆንዋ ታውቋል።
የኬንያ ጠቅላይ ካቢኔ ፀሃፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ እንዳሉት በርካታ የአፍሪካ መንግስታት የአህጉራዊው ህብረት ቀጣዩ ሊቀመንበር ከምስራቅ አፍሪካ እንዲሆን ተስማምተዋል ማለታቸው ተሰምቷል።
የቀድሞው የኬኒያ ጠቅላይ ሚንስትር እና አንጋፋው ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ቀጣዩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር እና ሊቀመንበር እንዲሆኑ ዘመቻ መጀመራቸውንም የኬኒያ መገናኛ ብዙሃን በስፋት እየዘገቡ ነው።
የአፍሪካ ኀብረት አስፈጻሚዎች ምክር ቤት 22ኛ ልዩ ስብሰባው በቀጣዩ ዓመት ለሚደረገው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ከፍተኛ አመራር ምርጫ ዝግጅትን አስመልክቶ የቀረበውን ሪፖርት መርምሮ የተለያዩ ማስተካከያዎችን በማከል በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
በዚሁ ለአንድ ቀን በተካሄደ ልዩ ስብሰባ የሞሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ መሃመድ ሳሌም ኦሉድ (ዶ/ር) በመድረኩ እንዳሉት፤ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ አፍሪካ በሰላምና ደኀንነት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ በመፍጠር ረገድ የሚኖራትን ሚና የሚያሳድግ ሊሆን ይገባል። ማለታቸው ተነግሮል።
በስብሰባው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማት፣ የኅብረቱ የወቅቱ ሊቀ-መንበር ሞሪታኒያ – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ሞሃመድ ሳሌም ኦሉድ የኅብረቱ ኮሚሽነሮች፣ ሚኒስትሮችና የተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።en