የአደዋ ድል በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ ነው፤ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ አደዋ ናቸው 

የአደዋ ድል በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ ነው፤ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ አደዋ ናቸው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||124ኛው የዓድዋ የድል በዓል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በዓድዋ ተከበረ። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችም በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በአዲስ አበባ የንጉሰ ነገስቱ ሐውልት በሚገኝበት አደባባይ በተገኙ በርካታ ወጣቶች ልዩ ልዩ ትርኢቶችን አሳይተዋል።

በታሪካዊው አደዋ ከተማም መታሰቢያ በዓሉ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተከብሯል።

የድል በዓሉ የጣሊያን ወራሪ ድል በተደረገበት የዓድዋ ተራሮች ሥራ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች  ተከብሯል።  በዚህ በዓል በሥነ ሥርዓቱ ላይም አርበኞች፣ ወጣቶች፣ ህፃናት እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሐላፊዎች ተገኝተዋል። የድል በዓሉን የሚያስታውሱ ሙዚቃዊ ድራማዎች እና ሌሎች ዝግጅቶች ቀርበዋል።

LEAVE A REPLY