ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ያለ ሕጋዊ ፈቃድ በጎንደር ከተማ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጡ ነበር ተብለው የተጠረጠሩ 13 ካናዳውያን በቁጥጥር ሥር የዋሉት።
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ አርብ የካቲት 20/2012 አንድ የካናዳ ግብረ ሠናይ ድርጅት 13 ሠራተኞቹ ጊዜው ያለፈበትን መድኃኒት ሲያሰራጩ እንደነበር ተጠርጥረው በቁጥጥር መዋላቸውን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል:: ተጠርጠረው ከታሠሩት መካከል ኹለት ኢትዮጵያውን ሠራተኞች እንደሚገኙበት ተነግሯል።
የካናዳው ግብረ ሠናይ ድርጅት በበኩሉ ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑት ባለሙያዎች የተማሩ እና ብቃት ያላቸው መሆኑን በመግለፅ በካናዳ ሲሰጡት ከነበረው የሕክምና አገልገሎት የተለየ አልሰጡም ሲል በድኅረ ገጹ ላይ አስታውቋል። በጉዳዩ ላይ የካናዳ እና የኢትዮጵያ መንግሥት ሊነጋገሩበት እንደሚችሉ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
እስከ አሁን ሃገራቱ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጡም። የካናዳ አለማቀፍ ዲፓርትመንት ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን ገልጿል።

























