በአዲስ አበባ ኤልፓ የቤት ለቤት ቆጣሪ ንባብ ላቆም ነው አለ

በአዲስ አበባ ኤልፓ የቤት ለቤት ቆጣሪ ንባብ ላቆም ነው አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዲስ አበባ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን መስፋፋትን ተከትሎ የድርጅቶችናንና የቤት ለቤት የሚደረግ የቆጣሪ የንባብ ሥርዓት ሊቀር ነው ተባለ።

የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ድርጅት የዲስትሪቢዢን ሲስተም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ   ወረርሽኙን ተከትሎ በአሁን ወቀት በአንባቢ በኩል በየቤቱ እየዞረ የሚደረግ የቆጣሪ ንባብ ሥራ፣ ንክኪ ሳይኖረው አካላዊ እርቀተን ጠብቆ አንብቦ መሄድ ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ።
ሆኖም በተገልጋይ በኩል አንባቢ ወደ ቤቱ እንዲመጣበት አይፈልግም የሚሉ ስጋቶች በመኖራቸው፤ ድርጅቱ አስቀድሞ ይህን ስጋት ለማስቀረት አሠራሩን ለማሻሻል ማቀዱን ጠቁመው፤ በአዲሱ አሠራር የቤት ለቤት ንባብ እንደሚቀር፣ የድርጅትንና የቤት ለቤት የሚደረግ የቆጣሪ የንባብ ሥርዓትን ለጊዜው በማስቆም፣ ደንበኞች ባለፉት ሥድሥት ወራት ሲጠቀሙበት በቆየ የኤሌትሪክ አጠቃቀምን ንባብ ታሳቢ ተደርጎ እንዲከፍሉ ይደረጋል ሲሉም አብራርተዋል።
በተቀጠሱት ጊዜያት እላፊ የከፈለ ደንበኛ በሚቀጥለው ወር የሚስተካከልለት ሲሆን በተጠቀመበት ልክ ያልከፈለም በተመሳሳይ በቀጣይ ወር እንዲከፍል ይደረጋል የሚሉት የኤሌክትሪክ ኃይል ሓላፊው፤ ይህ አሠራር በቀጣይ ወሮች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መስፋፋትን ተከትሎ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።
 የኢትዮጲያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ድርጅት ደንበኞች በቤታቸው ሆነው በድረ ገጽጽ ያለፈ ታሪካቸውን የሚያነቡበት እና አገልግሎት የሚያገኙበት የኦላይን አሠራር ለመተገበርም እየሰራ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።
በዚህም የድህረ ገጽ አገልግሎት ለማመልከቻ ፣ ክፍያ ለመክፈልም ሆነ እየሰራን ነው ያሉት  አመራሩ አገልግልት አሰጣጥን የማዘመን ሥርዓት በቀጣይ ለደንበኞች ይፋ እንደሚደረግ ጠቁመው፤ ተቋሙ ወረርሽኙን ተከትሎ የፋይናንስ ጫና እንደገጠመው፣  በዚህም ቀደም ሲል ከደሞዝ ውጪ በትርፍ ሰዐት ይከፍል የነበረውን የሠራተኛ ከፍያ ለማስቀረት መገደዱን ገልጸዋል።
በሌላም በኩል ተቋሙ የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል የደንበኞቹን ጤንነት ለመጠበቅ የተለያዩ አሠራሮቹን በማዘመን ደንበኞቹ በድረገጽ ወይም በአላይን የሚጠቀሙበትን አሠራር ለመዘርጋት እየተጋሁ ነው ሲል ተደምጧል።
መ/ቤቱ በአሁን ሰዐት ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ሲኖሩት፤ ከእነዚህ ደንበኞ መካከል በነባሩ ቆጣሪ አገልገሎት የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቋል።

LEAVE A REPLY