በቃ! ይሁን አሜን || ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

በቃ! ይሁን አሜን || ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

 የኢት ኢል ኢያን ን አ ናይ

ዝም! እንዳይታረቁ ሆነው የተጠመዱ፥ እንዳይፈታ ሆኖ የተቋጠሩ፥ እንዳይታይ ሆኖ የተሰወሩ ትርክቶች ታት ልን! ያልተፈታን ቋጠሮን መፍታት፥ ያልታሰበን አስተሳሰብ ማሰብ፥ ያልተሄደበትን መንገድ ን።

የሕዝቡ ነት የሚገርም ነው። በመሪዎቻችን ማንነት ሕዝቡ ማንነቱን ተጠልፎ መነጋገሪያ የሆነው ክትነው። ማን ያውራ ስለ ደጉ ሕዝብ? ማን ያውራ በፍቅር ስለሚተሳሰበው ሕዝብ? ሲራብ አብልቶ፥ ሲጠማ አጠጥቶ፥ አብሮ ተቻችሎና ተጋብቶ ዘመናት የሚኖረውና የሚያኖረውሕዝብ ማን ማንነቱን ያራግብለት? ያደከመን በመሪዎቻችን ማንነት ላይ የተመሰረተ የፊት ለፊት እያወራን ስጋታችንመብዛቱ ነው። ሁሉ ላማውን የሚያራምደው ኢትዮጵያን የመሪዎቻችን ነፀብራቅ አድርጎ በመውሰድ ነው ከላይ ላይከሚታየ ጀርባ የተደበቀውና በጊዜ ተፈትኖ ያለፈው ትልቁጥል እውነት ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቤተሰብነት ነው።

እኛ የወለድናቸው ልጆቻችን ለኢትዮጵያ ምን ሊያደርጉ ይቻላሉ ተብሎ ቢታሰብ ከአዕምሮ በላይ ነው። ልጆቻችን የእኛን መባላት ከማየት ይልቅ ፍቅራችንንና ሰላማችንን እንዲያዩ ብንፈቅድላቸው እነሱ ለኢትዮጵያ ለመድረስ ይበቃሉ። እኛ ሁሉን አይተን የዕድላችንን ሞክረን አንገት ለአንገት ተያይዘን ከመሬት አልተነሳንም። አሁን ግን ለልጆቻችን ዕድል ፈንታ እንሰጥ ይሆን? ዛሬ አዲስ ጅማሬ አቅቶን ተቸገርን። ነገር ግን ሌላው ቢቀር ነገ ልጆቻችን ኢትዮጵያን ሳትሰነጣጠቅ ማስረከብ እንኳን ብንችል፥ እነርሱ አዲስን ነገር ያሳዩን ነበር። ታዲያ ካለንበት አዘቅት ለመውጣት መተባበር አቅቶን ይህችን ኢትዮጵያ ሀገር እንዳትሆን እያደረግናት ይሆንን? እንው አ አመት እንኳን ወስዶብን ከድሮ የተለየ አሰራርና አስተሳሰብ ለማሳየት ችለናልን? እንው ይህችን ሀገር አጥፍተን ካልጠፋን አንነቃምን? ልጆችን የራሳቸው እድል እንዳይሞክሩበት መና ልናስቀራቸው ነውን?

ኢትዮጵያ የሕዝቡ ውጤት እንጂ የመንግስታት ፍሬ አይደለችም። መንግስት ይመጣል፥ ደመጣም ይሄዳል። ቋሚ ነገር ዝቡ ነው። እውነተኛውና የሚፀናውን ኢትዮጵያዊነት የሚያረጋግጠው ሕዝብ ነው። የኢትዮጵያ ጠባቂ ሕዝብ ነው። ኢትዮጵያ ሕዝቡን ስለሚወክል በራሱ እፁብ ድንቅ ነው። ዝቡ የኢትዮጵያን የነገውን እጣ ፈንታ ይወስናቅ አ(ከአና)። ኢ ለ ኢ ግ አቀቅ ባው

ዎች ትርክት ይዘን ሰጣ ገባ ስንገባና ኢትዮጵያን ጥያቄ ውስጥ ስናስገባ፥ እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት ለመቀበል እድልና ፈንታ እንዳይኖረን እያደረገን ነው። ይህንንም ስናደርግ ኢትዮጵያን ጥያቄ ውስጥ ማስገባታችን ዝቡ ራሱን ጥያቄ ውስጥ ማስገባታችን እንደሆነ ስለማናስተውል ነው። ለዚህም ስህተት የሚዳርገን፥ ትርክታችንንቱት መንግስታት ባደረጉት ድርጊት ላይ የንን ኢትዮጵያን ተመርኩዘን ስለሆነ ነው። ይህን ስናደርግ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያነትን ከዝቡ ነጥለን መንግስታትን የኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ ፈጣሪ አድርገን መፈረጃችን እንደሆነ ይታወቅ። ይህን በማድረጋችን፥ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊነት ዝቡ ያለውን አብሮነት ዋናውን ስፍራ አለመስጠት ይሆንብናል። የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ፅናት ግን የሕዝቡ ውጤት ነውና ሕዝብ እስካለ ድረስ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል። እውነተኛው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ቃን በራሳቸው ዕይታ የሚስሉት ማንነት አይደለም። በራሱ በሕዝቡ የተገነባ ከመንግስታት ተነጥሎ በራሱ የቆመ ማንነት ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ፈተና ላይ ስም

እውነተኛው ኢትዮጵያዊነት እኛ ወይም ሌላው በፍልስፍና የሚፈጥረው ነገር ሳይሆን፥ ራሳችንን (ዝቡን ማንነቱን) የሚተርክ እውነታ ነው። ያም የተዋበና የሚገርም ነው። እውነታው ስለ ሕዝቡ ናገራል። የኛ ጥረት የን መነፅር ከአይናችን ላይ አውልቀን የሕዝቡን ውበት እንደ ነበረና እንዳለ መመልከት መቻል ላይ ነው። ያኔ የተሰወረውን እውነተኛውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማወቅና ለማሳወቅ ይቻለናል።

እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነትን ለመተዋወቅ ከሕዝቡ እንጀምር። ሕዝቡ እውነተኛ ቅንና በጎ ነው። በጎና መልካም የሆነው ይህ ሕዝብ ማንነቱን ለማንፀባረቅና እርሱነቱን ለማብራት ያልቻለበት ሁኔታ ውስጥ ነው ለዘመናት ያለው። ኢትዮጵያዊነትን ከሕዝቡ ስብዕና ላይ ተመርኩዘን ለማወቅ ብንጥር ቤተሰብነትን ያሳየናል። ስለዚህ ጥረታችንና ሕልማችን ይህንን እውነተኛውን ማንነታችንን ለማወቅ ይሁን። ልዩነታችን ውበታችን ሆኖ ይታየን። እኩልነት የእውነተኛ ኢትዮጵያዊነት ስርና መሰረት እንደሆነ ይታወቀን። ራዕያችን እንደሆነው እንድንታወቅ ይሁን። እንደ ማንነታችን ሁሉ አቅማችንም ያንን ያህል ታላቅ መሆኑ ይግባንና ለካ ምንም አልሰራንም ብለን እንቆጭ። በዚህም ቁጭት እውነተኛውን ራሳችንን ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን እውነተኛው አቅማችንንም መግለጥ ይብዛል

እስቲ የራሳችንን እውነተኛውን ማንነት ማወቅና መረዳትን እናስቀድም። የቤት ስራችን ኢትዮጵያዊነትን ማፍረስ ሳይሆን ያልተገለጠልንን እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነትን ማስተዋል ላይ ያተኩር። ዎች የሚስሉት ኢትዮጵያዊነት ላይ ተወስነን ኢትዮጵያዊነትን አንኮንን። ይልቁንም በሕዝቡ ልብ የተሰወረውንና በየዕለት ኑሮው የሚተገበረውን ኢትዮጵያዊነት ከሽፋኑ አውጥተን ለዓለም ለማሳየት እንጣር። ፍርሃት ሳይሆን ፍቅር የሚገዛው እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት እናውጅ። አለመተማመን የሚነዳንና የሚያናቁረን እንዳይሆን እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነትን ማወቅ ቤተሰብነታችንን አስረድቶን አዲስ ምዕራፍ ይክፈትልን። ቁምነገሩ ኢትዮጵያዊ ለመሆን የምንጥር ሳንሆን፥ ኢትዮጵያዊ ስለሆንን ያንን የማወቅ ጉዞ ላይ መሆናችንን ማስተዋል ላይ ነው። የሆንነውን ሆነን ለመገኘትና የተሰወረውን እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነ በገሃድ ለመግለጥ ራሳችንን እናነሳሳ።

የኢትዮጵያ አንድነት የሚመነዘረው በሕዝቡ አንድነት እንአይደለም። እርስ በርስ መያያዛችን ከራሳችን ከውስጥ የመነጨ ነው እንጂ ከውጭ ሌላው የሚጭንብን መከናወን አይደለም። ዎች በኢትዮጵያዊነት ላይ የጣሉትን ሽፋን ገልጠን፥ እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት በማንፀባረቅ እንደ ሆንነው በዚያኑ እንድንታወቅ ራዕያችን ይሁን። ያም ለዓለም ድንቅና መገረም እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያዊነት ላይ ጎራ ይዘን ከምንተራመስ፥ እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት ከሕዝቡ የምንማርበትን ሂደት ላይ ግድ ቢለን መልካም ይሆንልናል። ይህ ቢበዛልን፥ የአፍሪካ ኩራት የሆነችው ኢትዮጵያ የዓለም ተስፋ እንድትሆን በር ይከፍትላታል። ስለ አንድ ኢትዮጵያ ከመጨቃጨቅ አልፈን ስለ አንድ አፍሪካ ፈር ቀዳጆች ለመሆን እንድንታደል ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ነገር እንቆቅልሿ የሚከብደው ጉዳዩ የውስጥ ብቻ ስላልሆነ ነው። ለሁሉ ነገር ወዳጅና ጠላት እንዳለ ሁሉ፥ ኢትዮጵያም ወዳጅና ጠላት አላት። አሻፈረኝ ብላ የጥቁር ሕዝብ ተስፋና ኩራት መሆኗን የሚያደንቁ እንዳሉ ሁሉ ነርቫቸውን የሚነካም አይጠፋም። የብዙዎች መተዳደሪያ የሆነው የውሃ ስርና መሰረት ጥንስሱ አባይ ከኢትዮጵያ ስለሚነሳ በዓይነ ቁራኛ መታየቷ አይቀሬ ነው። በዙሪያዋ እየተተራመሱ በመካከል እንደ ወጥ ቁጭ ብላ በእድገት ልትመነጠቅ የምትንደረደር ኢትዮጵያን ማየት የማይመቻቸው ይኖራሉ። በተለይ ሽብርተኛውን ከአሜሪካ ጋር እየተባበረች በአካባቢዋ አከርካሪ ሰባሪ መሆኗ ጥቁር ነጥብ በጠላቶች ዘንድ ማስጣሉ አይቀርም። ምዕራቡ ዓለም ከእጅ ወደ አፍ እርዳታ እያደረገ ለዘመናት ኖሮ ሳለ ዛሬ ቻይና በኢኮኖሚው ላይ ጫና ያለው የመሰረታዊ ልማት እንቅስቃሴ እንድታደርግ በተደረገውም ስራ ኢትዮጵያ ከተኛችበት የተነሳች እስክትመስል የሚታይበት ሁኔታ ሌላ ጠላትነት የሚያፈራ ሊሆን ይችላል። ይህ እንግዲህ በውስጥ በራሳችን ልጆች ከሚመጣው አለመግባባት መዘዝ ከሚደረገው የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው አካሄድ ጋር ሲደመር ነው ቋጠሮዋ የሚጠቀው

የኢትዮጵያ ቋጠሮ ባለን ሁኔታና በሚጠብቀን ዕድል መካከል ያለው ውጥረት ነው። ያለንበት ስፍራና ልንሆንበት የሚጠራን ከፍታ አይገናኙም። በአንድ ዓይነት ሃይማኖትና በአንድ አይነት ብሔር የተዋቀረችው ሶማሊያ ከመፈራረስ አንድ አይነት መሆኗ አላዳናትም። አሜሪካ በሌላ በኩል ከዓለም ዘር ሁሉ የተውጣጡ ሕዝቦችን ይዛ በእግዚአብሔር ስር ያለ አንድ ሕዝብ ያውም ሊከፋፈል የማይችል በማለት ይምላሉ። ልዩነትን አስተናግደው ከዓለም የሚያስንቅ ዲሞክራሲን ለማራመድ ችለዋል። ይህ ሁሉ የሚያሳየን እንደ ትልቅ ነገር ይዘን የምንቆራቆስበት ትርክቶችከመጠላለፍ ያለፈ ያደረገልን ነገር የለም።

ሕገ መንግስታችን የትላንትን ፍርሃት የሚናገር እንጂ የነገን ራዕይ የሚያውጅ አይደለም። ትላንት ስለተበዳደልን ዛሬ እስከ መገንጠል የሚል መብት አስቀመጥን። የምንተነብየው ያ ነገር ይሆናል። ዛሬ ላይ ቆመን ነገን ስናይ ምን ይታየናል? ፍርሃታችን ሳይሆን ተስፋችን እንዲመራን ለምን አላረግንም? አንድ ሕዝብ ተብለን የሕዝቦች መብት አለመጠበቁን ለማስመር ሕዝቦች ብለን ለምን እንደመድማለን? ለመሆኑ ተጋብተን ተዋልደን የኖርን አይደለምን? መሬት ታች አውርደን ካየን እንደ ወንድምና እህት ተከባብረን ስንቱን አብረን አሳለፍን? ደግነት እና ትህትናችን ለምን ዋጋ አጣ? አብረን ደምተን ዳር ድንበርአስጠብቀን፥ እስላምና ክርስቲያን ተባብለን ሳንገፋፋ አብረን ስንቱን አሳለፍን? መንግስታት ሲቀያየሩብን ድህነት እና ችግርን እርስ በርስ ባንረዳዳ እዚህ እንደርስ ነበር ወይ? ን ኢያ አም አና።

ብዙ ሰው መላ ሲሰጥ ይታያል። ያ መላ መልካም ሆኖ ሳለ፥ ጆሮ ሰሚ ሳያገኝ በግራና በቀኝ መንገድ ላይ ወድቆ ባከነ። ችግራችን የመፍት እጦት አይደለም። የመግባባት መተላለፍ እንጂ። ስለዚህ መግባባትን ከመጨረሻው ላይ ቆመን ከመፍትው ጎራ ከመፈለግ፥ ግና ከመጀመሪያው ከችግሩ ጥንስስ ላይ ቆመን የችግሩን ስም በማውጣት ላይ እንስማማ። የችግራችንን ስም ሁላችንም የተስማማንበትን ስም አውጥተን ስናበቃ ያ የችግሩ ግንዛቤ መግባባት አንድ ቋንቋ ይሰጠናል። ያኔ ችግሩ ላይ ከተስማማን ሁላችንም ከአንድ ስፍራ እንጀምራለን ማለት ነው። በአንድ ስፍራ ለመሆናችን ምክንያቱ መላ ስላገኘን ሳይሆን ቋጠሮውን በአዲስ ግንዛቤ ስለገነባነው ነው። ያኔ ሁላችንም ቋጠሮውን ለመታት ከአንድ ስፍራ ስለምንነሳ ወደ አንድ አቅጣጫ ለመሳተፍ ይቀላል።

ኢትዮጵያ የታሪክ እስረኛ አይደለችም። ምክንያቱም ከታሪክ ተምረን አዲስን አቅጣጫ ለነገ ዛሬ መተለም ይቻለናልና። የኢዶ/ር አቃ!ን አሜን ው።

LEAVE A REPLY