ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ወድቆ የተገኘ ቦንብ ፈንድቶ በአንድ ግለሰብ ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተረጋገጠ።
ዛሬ ህዳር 2 ቀን ጠዋት 2 ሰዐት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አድዋ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የተጠቀሰው የቦንብ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።
በቦንቡ ጉዳት የደረሰበት አንድ የታክሲ ረዳት እንደሆነም ከትክክለኛው መረጃ መረዳት ተችሏል።
ግለሰቡ በደረሰበት ጉዳት በምንሊክ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተለ የሚገኝ ይገኛል። የታክሲ ረዳት የሆነው ወጣት ለመፀዳዳት ወደ ድልድዩ እንደገባና በማዳበሪያ የተጠቀለለ እቃ ተመልክቶ በእግሩ መርገጡንና ከዚያ በኋላ ራሱን እንደሳተ መናገሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

























