ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዘርፍ ስኬታማ አትሌቶችን በማበርከት የሚታወቀው የዲባባ ቤተሰብ አዲስ ኮከብ ይዞ ብቅ ማለቱ ተሰምቷል።
ትናንት በስፔን ባርሴሎና በተደረገው የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ገንዘቤ ዲባባና ታናሽ እህቷ አና ዲባባ ውድድሩን 1ኛና 2ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።
ገንዘቤ ውድድሩን ለመጨረስ የፈጀባት ጊዜ 15:00 ሲሆን፣ አዲሷ ተስፈኛ አና ዲባባ ደግሞ 16:02 በሆነ ጊዜ ውድድሩን ማጠናቀቋ ታውቋል።

























