ጥቅም ላይ እንዳይውል ከተከለከለ 50 ዓመት የሞላው ዲዲቲ ኬሚካል ማምረትን ኢትዮጵያ አቆመች

ጥቅም ላይ እንዳይውል ከተከለከለ 50 ዓመት የሞላው ዲዲቲ ኬሚካል ማምረትን ኢትዮጵያ አቆመች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ለጤና አደገኛ በመሆኑ በመላው ዓለም  ጥቅም ላይ እንዳይውል ከተከለከለ ከ50 ዓመት በላይ የሆነው ዲዲቲ የተባለው ኬሚካል እጅግ ቢዘገይም በኢትዮጵያ ሥራ ላይ እንዳይውል ተከለከለ።

ይህ ኬሚካል በተለይ ይመረትበት በነበረው በአዳሚ ቱሉና አዳማ በሚገኘው ዋናው መጋዘን ይገኛል የተባለው ብዙ ሺህ ቶን ኬሚካል ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይሰራጭ መከልከሉን የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
አደገኛ የተባለውን ዲዲቲ ኬሚካል ወደ ውጭ ልኮ ለማስወገድ የሚያስችል ሥራ መጀመሩን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሯ ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ ፤ ኬሚካሎች የሚያስከትሉትን የአየር ብክለትና የጤና እክል ለመከላከል ከዚህ ዓመት ጀምሮ የኬሚካል ምዝገባ ሥራ ይጀመራል ተብሏል፡፡
የሀገር ቤት አምራቾችም ሆኑ ከውጭ ኬሚካል የሚያስመጡ ሁሉ ኬሚካሎችን እንዲያስመዘግቡም አዲስ ሥርዓት መዘርጋቱን እና ድርጅትች የሚያመረቱትም ሆነ ከውጭ የሚያስመጡትን ኬሚካል መቼ እንደተመረተ፣ የመጠቀሚያ ጊዜው መቼ እንደሚያበቃ እንዲያስመዘግቡ እንደሚገደዱ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY